fbpx

አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ በአፍሪካ ህብረት የተመድ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ሆነው ተሾሙ

አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ በአፍሪካ ህብረት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጽህፈት ቤት ሀላፊ ሆነው ተሾሙ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴን በአፍሪካ ህብረት ልዩ ተወካያቸው እና በአፍሪካ ህብረት የተመድ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አድርገው ነው የሾሟቸው።

በዚህም መሰረት አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ የስራ ጊዜያቸው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ሰኔ 23 2018 የሚያበቃውን አቶ ሀይሌ መንከሪዮስን የሚተኩ ይሆናል።

አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከመጋቢት 2011 ጀምሮ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የናይሮቢ ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር ጀነራል በመሆን በማገልገል ላይ ነበሩ።

በተጨማሪም አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ዘርፍ በዲፕሎማትነት እና በተለያዩ የሀላፊነት ስራዎች ላይ ማገልገላቸውን ተነግሯል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram