fbpx

አሜሪካ “C-130” የተባለ ወታደራዊ አውሮፕላን ለኢትዮጵያ አበረከተች

የአሜሪካ መንግስት “C-130” የተባለ ወታደራዊ አውሮፕላን ለኢትዮጵያ አየር ሀይል አበረከተ።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ አውሮፕላኑ በትናንትናው እለት ነው በቢሾፍቱ ከተማ ለኢትዮጵያ አየር ሀይል የተበረከተው።

ወታደራዊ አውሮፕላኑ ርክክብ ላይም የአሜሪካ መንግስትን በመወከል በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ራይነር እንዲሁም በኢትዮጵያ በኩል የኢትዮጵያ አየር ሀይል አዛዥ ጄነራል አህመድ መሃመድ ተገኝተዋል።

በርክክቡ ወቅትም “C-130” የተባለው ወታደራዊ አውሮፕላን ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላምን ለማስከበር የምታደርገውን ጥረት የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

በተለይም ኢትዮጵያ በጦርነት ምክንያት ለተጎዱ ንጹሃን ሰዎች አስፋላጊ የሆኑ ሰብአዊ ድጋፎችን በፍጥነት እንድታደርስ እና በግጭት አካባቢ የሚኖሩ የንጹሃን ዜጎችን ህይወት ለመጠበቅ የምትሰራውን ስራ የሚደግፍ ነው።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ራይነር በርክክቡ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ወታደራዊ አውሮፕላኑ ለኢትዮጵያ መበርከቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት የሚያሳይ ነው ብለዋል።

የአሜሪካ መንግስት የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ከዚህ ቀደም ከነበረው የበለጠ እንዲጠናከር ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ያሉት።

በአፍሪካ እና አውሮፓ የአሜሪካ አየር ሀይል ብርጋዴር ጄነራል ዲተር ባሬሂስ በበኩላቸው፥ “C-130” የተባለውን ወታደራዊ አውሮፕላን ለኢትዮጵያ በማበርከታችን ደስታ ይሰማናል ብለዋል።

አውሮፕላኑ ለኢትዮጵያ መበርከቱ በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለው ግንኙነት የሚያጠናክር መሆኑን ገልፀው፥ ለአዳዲስ የትብብር መስኮችም መሰረት የሚጥል መሆኑን ተናግረዋል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram