አሜሪካ በኢራን ባለሀብቶች እና ኩባንያዎች ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ጣለች

አሜሪካ ከኢራን አብዮታዊ ዘብ ጥበቃ ወታደራዊ ባለስልጣናት ጋር ግንኙነት አላቸው ባለቻቸው ስድስት ግለሰቦች እና ሶስት ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታወቀች።

ማዕቀቡ የተጣለባቸው አካላት በርካታ ሚሊየን ዶላሮችን ለአብዮታዊ ዘብ ጥበቃ ወታደራዊ ባለስልጣናቱ ድጋፍ አድርገዋል የተባሉ ናቸው።

የኢራን ማዕከላዊ ባንክ የአብዮታዊ ዘብ ጥበቃ የአሜሪካ ዶላር በከፍተኛ መጠን እንዲያዘዋውር ማድረጉን የአሜሪካ ግምጃ ቤት አስተዳደር ጸሀፊ ስቴቨን ምኑቺን ተናግረዋል።።

በትራምፕ አስተዳደር ማዕቀቡ የተጣለባቸው ስድስቱ ሰዎችም ኢራናውያን መሆናቸው ተነግሯል።

ማዕቀቡን ተከትሎ ከተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና ከኢራናውያን ጋር የንግድ ሽርክና የነበራቸው አሜሪካውያን የንግድ አካላት በጥምረት እንዳይሰሩ መታገዳቸውም ታውቋል።

እርምጃው የኢራን መንግስት እና ማዕከላዊ ባንኩ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በኩል የአሜሪካ ዶላር እንዳያገኙ በማድረግ የአብዮታዊ ዘብ ጥበቃ ድጋፍ እንዳያደርግ የሚያስችል ነው ተብሏል።

የዚህ ማዕቀብ አላማ የአብዮታዊ ዘቡን የዶላር ምንጭ መዝጋት እንደሆነም ስቴቨን ምኑቺን ገልፀዋል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው ከ2015ቱ የኢራን የኒውክሌር ስምምነት መውጣቷን ከትናንት በስቲያ መግለጻቸው ይታወሳል።

ከስምምነቱ ለመውጣት በዋነኛነት ምክንያት ያደረጉት የቀድሞው ስምምነት ኢራን የኒውክሌር ባለቤት እንድትሆን ያስችላታል የሚል ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram