አልጄሪያ ከ13 ሺህ በላይ ስደተኞችን ወደ ሰሃራ በረሃ እንዲመለሱ አድርጋለች

አልጄሪያ ባለፉት አስራ አራት ወራት ከ13 ሺህ በላይ ስደተኞችን ከሃገሯ በማስወጣት ወደ ሰሃራ በረሃ እንዲመለሱ አድርጋለች ተባለ፡፡

ሀገሪቷ ነፍሰጡሮችን፣ ህጻናት እንዲሁም ሌሎቹንም ስደተኞች ያለምግብና ያለውሃ ወደ ባዶ በረሃ ማባረርዋ እያስተቻት ይገኛል፡፡

ሰሃራ በረሃ ሙቀቱ 48 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ይደርሳል የተባለ ሲሆን፥ በሙቀቱ ሳቢያም ብዙዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

የአይን እማኞቹ እንደሚሉት ከሆነ ልጆቻቸውንና ወላጆቻቸውን ያጡ ይገኙበታል ብለዋል፤ ከዚህ ሁሉ የሚከፋው ደግሞ በረሃ ላይ የወለዱ መኖራቸውንም ገልጸዋል፡፡

አንዳንዶቹንም የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ከበረሃ ላይ አግኝቶ አንስቷቸዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ቃል አቀባይ አልጄሪያ በስደተኞች ላይ የምትሰራውን እናውቃለን ሉዓላዊ ሀገር እንደመሆኗ መጠን የዓለም አቀፉን ህግ ካከበረች ስደተኞችን ከሀገሯ ማስወጣት ትችላለች ብለዋል፡፡

አልጄሪያ ስደተኞችን በገፍ ማስወጣት የጀመረችው ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ሲሆን፥ የአውሮፓ ህብረት ስደተኞችን በተመለከተ በሰሜን አፍሪካ ሀገራት ላይ ጠንከር ያለ ግፊት ማሳደሩን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

 

ምንጭ፦አልጀዚራ
በአብርሃም ፈቀደ

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram