fbpx

አልጄሪያ፣ ቱኒዚያና ግብፅ በሊቢያ ጉዳይ ላይ ውይይት እያደረጉ ነው

የአልጄሪያ፣ ቱኒዚያ እና ግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሊቢያን የእርስ በእርስ ግጭት ለማስቆም በተከናወኑ ስራዎች ዙሪያ የሶስትዮሽ ውይይት እያካሄዱ እንደሆነ ታወቀ።

በዚህ የሶስትዮሽ ውይይት በሊቢያ የህግ መንግስት ማሻሻያ በሚደረግበት ዙሪያ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዓመቱ መጨረሻ በሀገሪቱ የፓርላማ እና ፕሬዚዳታዊ ምርጫ እንዲከናወን የያዘውን እቅድ ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ከዚህ ባለፈ በሊቢያ የተለያዩ አቋም በያዙ ፓርቲዎች መካከል የሚደረገው የሰላም እና የእርቅ ድርድር ስለሚጠናከርበት ሁኔታም በሶስትዮሽ ውይይቱ የሚነሳ ነጥብ እንደሆነ ተጠቁሟል።

ይህ የሶስትዮሽ ውይይት በሊቢያ ውስጥ ያለውን የእርስ በእርስ ጦርነት ማስቆም በሚቻልበት ሁኔታ በየዓመቱ እንደሚካሄድ ተነግሯል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በዚሁ መድረክ ያዘጋጀውን ፍኖተ ካርታ በመጠቀም በሊቢያ ያለውን ግጭት ለማስቆም እያደረገ ያለውን ጥረት እና የመጣውን ለውጥ አቅርቧል።

ምንጭ፦ ሲጂኤን

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram