fbpx

አሊባባ ኩባንያ ከ100 የተለያዩ ሬስቶራንቶች ውስጥ የሚታዘዙ ምግቦችን ለደንበኞቹ በድሮን ያሉበት ቦታ ድረስ ማቅረብ ጀመረ

በቻይና ሻንግሃይ በበርካታ ዘርፎች በሀገሪቱ ተሰማርቶ ያለው አሊባባ ኩባንያ በድሮን አገልግሎት የታዘዘበት ቦታ ድረስ ምግቦችን ማቅረብ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

የሀገሪቱ መንግስት ከሻንጋይ ኢንዱስትራይል ፓርክ አቅጣጫ በሚገኙ 17 የተለያዩ መስመሮች ላይ እንዲሰራ ነው ፍቃድ መስጠቱ የታወቀው፡፡

እነዚህ 17 መስመሮች በጥቅሉ ከ 57 ስኬዌር ኬሎሜትር በላይ ይሸፍናሉ ተብሏል፡፡

ከኢንዱስትሪል ፓርኩ በሚገኙ 100 የተለያዩ ሬስቶራንቶች ውስጥ በአንዱ ደንበኞች ትዕዛዛቸውን ካስተላለፉ ከ20 ደቂቃ በኃላ ያሉበት ቦታ ድረስ ይሄድላቸዋል መባሉም ተነግሯል፡፡

ይህ በባህላዊ መንገድ ቀድሞ ቤት ለቤት ከሚያደርሱት ይልቅ ከገቢ አንጻር አዋጪነት ያለው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ድርጅቱ ባለፈው መስከረም ወር የሞከረው ኢ7 በመባል የሚጠራው የድሮን ሞዴል 6 ኪሎ የሚመዝን ምግብ ተሸክሞ 20 ኪሎሜትሮችን የሚጓዝ ሲሆን በሰዓት 65 ኪሎሜትር እንደሚጓዝ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

 

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram