“አሁን ያለው የፌደራሊዝም ሥርዓት የአማራውን ህዝባዊ አንድነት የሚገረስስ ሆኖ ነው ያገኘነው”

ላለፉት ቀናት የመስራች ጉባዔውን በባህር ዳር ከተማ ሲያከናውን የቆየው የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ፤ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን በመምረጥ ተጠናቅቋል። በዚህም መሠረት በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የሚያስተምሩት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔን የፓርቲ ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል።

የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ጉዳዮች ኃላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ ክርስቲያን ታደለን በፓርቲው ምስረታ፥ ቀጣይ እርምጃዎች እንዲሁም በተነሱ ትችቶች ዙሪያ ቢቢሲ አነጋግሯቸዋል።

ቢቢሲ- በቅርቡ መስራች ጉባኤያችሁን አካሂዳችኋል፤ ምን ይመስል ነበር?

አቶ ክርስቲያን ታደለ- ስብሰባው ከተጠናቀቀ በኋላ የስራ አስፈጻሚው ቁጭ ብሎ ተወያይቶ ነበር። ምስረታው ከጠበቅነው በላይ እጅግ ስኬታማ ነበር። ምስረታውም ትክክለኛ እንደነበረ አረጋግጦልናል። ይህ ጉዳይ የተወሰኑ አባላት ብቻ ጉዳይ አይደለም፤ በትንሹ ከ40 እስከ 45 ሚሊየን የሚገመተው የሁሉም አማራ ተወላጅ ጉዳይ ነው ብለን ነው የምናምነው።

በሃገራችን ህግ መሰረት አንድ ሃገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ሲመሰረት ቢያንስ 1500 አባላት ከአምስት ክልሎች ማስመዝገብ ስለሚጠበቅበት፤ እነሱን ነው ለምርጫ ቦርድ በመስራች አባልነት ያስመዘገብነው።

ቢቢሲ- የአጭር፤መካከለኛ እና የረጅም ጊዜ እቅዶቻችሁ ምንድናቸው?

አቶ ክርስቲያን ታደለ- እንግዲህ ሁሉም ሰው እንደሚከታተለው፤ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ በየጊዜው ተለዋዋጭ እና እጅግ ፈጣን፤ ጊዜ የማይሰጥና ሌት ከቀን መስራት የሚጠይቅ ነው ብለን እናምናለን።

የአጭር ጊዜ ግባችን ድርጅቱን ለህዝቡ ማስተዋወቅ ነው። አደረጃጀቱን በከተማ፤ በገጠር እንዲሁም ምሁራን አካባቢ ማጠናከር እናስባለን። በሃገር ውስጥም ከሃገር ውጪም ያለውን የአማራ ተወላጅ እናደራጃለን። ከዚያም ቀጥሎ ሊመጣ የሚችለው፤ እንደ ሃገር በአሁኑ ሰአት በጣም ፈጣን የሚባሉ ውሳኔዎች እየተወሰኑ ስለሆነ፤ አማራውን በቁመቱ እና በወርዱ ሊወክለው የሚችል የፖለቲካ ፓርቲ የለም ብለን እናምናለን።

ከዚህ በኋላ ማንኛውም አማራውን የሚመለከቱ ድርድሮች እና ጉዳዮች ላይ ህዝቡን ወክለን የመካፈል እንዲሁም የአማራውን ዘላቂ ጥቅሞች፤ፍላጎቶች እና መብቶችን ለማስከበር ጥረት እናደርጋለን።

በቀጣይ ደግሞ 2012 ላይ በሚካሄደው ሃገር አቀፍ ምርጫ ላይ እንሳተፋለን። በኛ እምነት የፖለቲካ ስልጣን ላይ ያለው ስርአት፤ አማራው እያጋጠመው ላለው የህልውና አደጋ ዋናው ምንጩ ነው ብለን ነው የምናስበው።

ስለዚህ በምርጫ የፖለቲካ ስልጣን ይዘን ይህንን የተዛባ ግንኙነት የማስተካከል ስራዎችን ለመስራት ነው የምናስበው።

ላፉት ሶስት አስርት አመታት ለሚጠጋ ጊዜ ስርአቱ ከተቀዳበት ህገ መንግስታዊ ድንጋጌው ጀምሮ አማራ ጠል እና ያገለለ እንዲሁም ህልውናውን የሚፈታተን ነው።

የረዥም ጊዜ እቅዳችን እነዚህን የህልውና ጥያቄዎች ማስከበር እና መሰል ተግባራት ወደፊት እንዳይፈጸሙበት የሚያስችል መዋቅራዊ ስርአት መገንባት ነው።

ቢቢሲ- በአጠቃላይ ህዝቡን ከመወከል አንጻር ምን አቋም አላችሁ? ምክንያቱም በስራ አስፈጻሚ ምርጫችሁ ወቅት ለሴቶች ብዙ እድል አልሰጣችሁም በሚል ቅሬታ እና ትችት ተነስቶባችሁ ነበር።

አቶ ክርስቲያን ታደለ- ይህ ቅሬታ በተለያየ መንገድ ለኛም ደርሶናል። በመሰረታዊነት የ13 ስራ አስፈጻሚ አባላት ምርጫ ነው የተደረገው። ከአስራ ሶስቱ ደግሞ አንዷ ብቻ ሴት ናት። ሌላው ደግሞ የሃይማኖት ጉዳይ ነው እየተነሳ የነበረው። መታወቅ ያለበት በመሰረታዊነት የህልውና ጉዳይ መሆኑ ነው።

ስለዚህ ሁሉም የተመረጠው በችሎታ እና በችሎታ ብቻ ነው። መሰረት ያደረግነው እሱን ነው። አንዱ አማራ ሁሉንም አማራ ይወክላል፤ ሁሉም አማራ ለአንዱ አማራ ዘብ ይቆማል በሚለው መርሃችን መሰረት ነው የምንሰራው። ለእያንዳንዱ የስራ ዘርፍ ብቃት ያላቸውን ሰዎች ነው የመለመልነው። የሴቶች ተሳትፎም ቢሆን፤ ከስራ አስፈጻሚዎች መካከል አንዷ ብቻ ሴት ብትሆንም፤ በርካታ ሴት መስራች አባላት እንዳሉን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን።

ቢቢሲ- አሁን ኢትዮጰያ ውስጥ ያለው ቋንቋ እና ብሄርን መሰረት ያደረገው ፌደራላዊ ስርአት ዙሪያ ምን አይነት አቋም ነው ያላችሁ? አማራ ክልልን እያስተዳደረ ካለው ፓርቲ ጋር ምን አይነት ግንኙነት እንዲኖራቹ ትጠብቃላችሁ?

አቶ ክርስቲያን ታደለ- የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ በመሰረታዊነት ፌደራላዊ ስርአትን አይቃወምም። ይህ ማለት ግን የአማራ ህዝብ ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ፌደራሊዝም ይደግፋል ማለት አይደለም። ለአብነት አሁን ያለው የፌደራሊዝም ስርአት የአማራውን ህዝባዊ አንድነት የሚገረስስ ሆኖ ነው ያገኘነው።

በዋነኛነት የመታገያ ጥያቄያችን የአማራን ህዝብ እንደ ህዝብ አንድነቱን እና የታሪካዊ ግዛት መብቶቹ እንዳይገረሰሱ እና እንዲጠበቅ ማድረግ ነው።

BBC Amharic

Share your thoughts on this post

 • IS IT REALLY DANGEROUS TO SLEEP WITH A CELL PHONE UNDER PILLOW?

  Since Cell phones have been invented, we have heard a lot about possible connection between brain cancer and cell phones. It […]

 • በህዳሴ ግድብ ሁለት ተርባይኖች በመጪው መስከረም ኃይል ለማመንጨት ዕቅድ አለ

  ዮሐንስ አንበርብር – ሪፖርተር የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለት ተርባይኖች በመጪው መስከረም 2011 ዓ.ም. ኃይል እንዲያመነጩ ዕቅድ መያዙን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ። የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት የሁለቱን ተርባይኖች ተከላ ለማጠናቀቅ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡ በመሆኑም በመስከረም ወር 2011 ዓ.ም.ተርባይኖቹ ኃይል ማመንጨት እንዲጀምሩ ዕቅድ ተይዟል። ሁለቱን ተርባይኖች ለማስጀመር ግድቡን በውኃ መሙላት የሚጠይቅ አለመሆኑን የገለጹትምንጮች፣ ግንባታው እየተከናወነ ተርባይኖቹ ኃይል ማመንጨት እንዲችሉ የሚያስፈልገውን የውኃ መጠን ማግኘት እንዲቻል ተደርጎ የግንባታ ዲዛይኑመሠራቱን ገልጸዋል። ግድቡ በአጠቃላይ 16 ተርባይኖች ሲኖሩት፣ በቅድሚያ ኃይል እንዲያመነጩ የታቀዱት ሁለቱ ተርባይኖች እያንዳንዳቸው 375 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅምአላቸው። በመሆኑም በመጪው መስከረም አገሪቱ ተጨማሪ 750 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል ስለምታገኝ፣ ይህም ጣና በለስና ተከዜ የኃይል ማመንጫግድቦች ተደምረው በአሁኑ ወቅት ከሚያመነጩት የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን እንደሚበልጥ አስረድተዋል። ግድቡ ሲጠናቀቅ 6,450 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም እንደሚኖረው፣ ይህም አሁን በአገሪቱ ያለውን ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም ወደ11 ሺሕ ሜጋ ዋት ኃይል ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል። የህዳሴው ግድብ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ዘርፍ ላይ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው፣ የአገሪቱን የኃይል ሥርጭት ከ41 በመቶ ወደ 75 በመቶ እንደሚያደርስምጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ የህዳሴ ግድቡ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ የሚይዝ በመሆኑ፣ ከዓባይ ተፋሰስ አገሮች በበለጠ ለዘመናት በብቸኝነት የወንዙ ተጠቃሚ የሆነችው ግብፅየውኃ ድርሻዋ እንዳይቀንስባት ሥጋቷን እየገለጸች ነው፡፡ ኢትዮጵያ የዓባይን ወንዝ ጥቅም ላይ ለማዋል ስትነሳም ሆነ እስካሁን የምታስረዳው በሌላ የተፋሰሱ ተጠቃሚ አገር ላይ ጉልህ ጉዳት ያለማድረስ መርህንነው፡፡ የግድቡን የውኃ አያያዝና አለቃቀቅ የተመለከተ ጥናትም በገለልተኛ አጥኚ ቡድን እንዲካሄድ መወሰኗም ይታወቃል። ላለፉት ሁለት ዓመታት በህዳሴ ግድቡ የውኃ አሞላልና አለቃቀቅ ጉዳይ ውይይቱ አሁንም እንደ ቀጠለ ሲሆን የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን ባለሙያዎችከመጋቢት 26 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በሱዳን ምክክር በማድረግ ላይ ነበሩ፡፡ የውይይቱ ውጤት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሦስቱም አገሮች መሪዎችእንደሚቀርብ ይጠበቃል።   Share your thoughts […]

 • Reconciling unity and diversity

  The centralized forms of government adopted in the past could not accommodate Ethiopia’s diversity and hence led to extended armed […]

 • Terhas Tareke – Bel Wesedeni ትርሃስ ታረቀ (ኮበለይ) በል ውሰደኒ – New Ethiopian Music 2018(Official Video)

  Share your thoughts on this post Share on FacebookShare on TwitterShare on Google+Share on LinkedinShare on PinterestShare on XingShare on […]