ናይጀሪያ በቺቦክ ልጃገረዶች የጠለፋ ወንጀል የተሳተፉ የቦኮ ሃራም አባላትን በቁጥጥር ስር ማዋሏ ተገልጿል።
የናይጀሪያ ፖሊስ በፈረንጆቹ 2014 የ276 የቺቦክ ልጃገረዶች የጠለፋ ወንጀል እጃቸው አለበት የተባሉ 8 የቦኮ ሃራም አባላትን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎች መካከል አንዱ የ23 ዓመት ወጣት የቺቦክ ልጃገረዶችን ጠለፋ ወንጀል ያቀነባበረው መሪ ስለመሆኑ የእምነት ቃሉን መስጠቱ በዘገባው ተገልጿል።
ከዚህም ሌላ ተጠርጣሪዎቹ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች 50 ያህል የአጥፍቶ ጠፊ የቦመብ ጥቃቶችን ማቀነባበራቸውንም ለፓሊስ ቃላቸውን ሰጥተዋል ተብሏል።
ቦኮ ሃራም በፈረንጆቹ 2009 ወታዳራዊ እንቅስቃሴ ከጀመረ ጊዜ ጀመሮ ለ20 ሺህ ያህል ሰዎች ሞትና ለ2ነጥብ3 ሚሊየን ያህል ዜጎች ከአካባቢው ለማፈናቀል ምክንያት መሆኑን ዘገባው ያስረዳል።
ከፈረንጆቹ 2014 ጀምሮ 2ሺህ ያህል ናይጀሪያአውያንም በቦኮሃራም ተዋጊዎች የተጠለፉ መሆኑንም ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት።
ምንጭ፦ aljazeera.com
የተተረጎመው፦ በእንቻለው ታደሰ
Share your thoughts on this post