የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ማዕከለ 3 ሚሊዮን ዓመት ካስቆጠረ የማርስ አለት በተገኘ መረጃ መሰረት ህይወት ያላቸው አካላት በፕላኔቱ ይኖሩ እንደነበር አመላካች መረጃ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡
ይህን እንጂ መረጃው ለተጨማሪ ምርምራ የሚጋብዝ እንጂ ማረጋገጫ የሚሰጥ አይደለም ተብሏል፡፡
ግኝቱ በማርስ ያለው የከባቢ አየር እና ተፈጥሮአዊ ነገር ህይወት ማኖር የሚያስችል እንደሆነ አመላካች ሆኗል፡፡
በማርስ ላይ የሚገኘው ሮቦት መሰል ተሽከረካሪ በላከው መረጃ መሰረት ማርስ ከቢሊዮን ዓመት በፊት ህይወት ማቆየት የሚችል የውሃ ክፍለ ነበራት፡፡
በመሆኑም አዲስ ጥልቅ ምርምር በማድረግ በማርስ ህይወት ያላቸው አካላት እንዲኖሩ ለማድርግ እየሰራ መሆኑን ናሳ አስታውቋል፡፡
ይሁን እንጂ ለመኖር አስፈላጊ የሆኑ ኦክስጅን እና ናይትሮጅን በስፍራው መገኘታቸው እስካሁን አልተረጋገጠም፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ እና ናሳ
Share your thoughts on this post