fbpx

ቻይናው ፕሬዚደንት ሺ ጂፒንግ አፍሪካን በመጎብኘት ላይ ናቸው

የቻይናው ፕሬዚደንት ሺ ጂፒንግ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ከትላንት በስቲያ ሴኔጋልን የጎበኙ ሲሆን በትላንትናው ዕለት ደግሞ ወደ ሩዋንዳ አቅንተዋል፡፡

ፕሬዚደንቱ ወደ ሩዋንዳ ሲገቡ በአቻቸው ፖል ካጋሚ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ሺ ወደ አፍሪካ ያደረጉት ጉብኝት በድጋሚ በፕሬዚደንትነት ከተመረጡ በኃላ የመጀመሪያ ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸው ሲሆን በጉዞዋቸው ላይም የተባበሩት አረብ ኤምሬት ገብተው የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

የሩዋንዳ ጉብኝታቸውን እንዳጠናቀቁ በብሪክስ ጉባዔ ላይ ለመካፈል ወደ ደቡብ አፍሪካ ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከጉባዔው ፍጻሜ በኃላ ሞሪሺየስን በመጎብኘት ጉብኝታቸውን ያጠናቅቃሉ ተብሏል፡፡

ቻይና በአሁኑ ወቅት ከአፍሪካ ጋር ጠንካራ የንግድ ግንኙነት የመሰረተች ትልቋ የንግድ አጋር ሆናለች፡፡

በፈረንጆቹ 2014 በወጣ መረጃ የቻይና-አፍሪካ የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነት 220 ቢሊየን ዶላር መድረሱን አመላክቷል።

የዓለም አቀፉ ኢንቨስትመንት ሪፖርት መረጃ እንደሚያመላክተው ደግሞ ወደ አፍሪካ የሚደረገው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በ2017 42 ቢሊየን ዶላር መድረሱን ገልጿል፡፡

 

 

ምንጭ፦ሽንዋ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram