fbpx

ቻይናዊው ግለሰብ ለ47 ዓመታት አንገታቸው ላይ አብሯቸው የቆየውን 15 ኪሎግራም ዕጢ አስወገዱ

ቻይናዊው ግለሰብ ለ10 ሰዓታት በዘለቀ ቀዶ ህክምና ለ50 ዓመታት አብሯቸው የቆየውን 15 ኪሎግራም ዕጢ ተወገደላቸው፡፡

ቻይናዊው ግለሰብ ሻ ሲንፉ ይባላሉ፤ ዕጢው ከ47 ዓመታት በፊት ሲጀምራቸው የእንቁላል ያህል ትንሽ ነበር ይላሉ፡፡

በዚያን ወቅት የሻ ሲንፉ ዕድሜ 17 ነበር፤ ታዲያ ህመም ስለማይሰማቸው በተጨማሪም ዕጢውን ለማስወገድ የሚያሰፈልገው ወጪ ውድ በመሆኑ ምክንያት ችላ አሉት፡፡

የሻ ሲንፉ ልጅ ከልጅነቱ ጀምሮ አባቱን የሚያወቃቸው አንገታቸው ላይ ትልቅ ዕጢ ተሸክመው መሆኑን ተናግሯል፡፡

ወደ እርጅናው ሲጠጉ ደግሞ በልጅነታቸው ህመም አልባ የነበረው ዕጢ ለመራመድም እያስቸገራቸው መምጣት ጀመረ፡፡

ታዲያ ልጃቸው ከህጻንነቱ ጀምሮ የሚያውቀውን ዕጢ ከአባቱ ላይ ለማስወገድ ያልም ነበር፤ በዚህም በቤተሰቡ እርዳታ ለህክምና የሚውል በቂ ገንዘብ አሰባስቦ ወደ ሆስፒታል ወላጁን ይዞ ማምራቱን ገልጿል፡፡

በመጨረሻም ወደ ግዊጆ የእጢ ማስወገጃ ሆስፒታል በዶክተር ዶንግ እርዳታ ቀዶ ህክምና ሊደረግላቸው ተወሰነ፡፡

ዶክተር ያንግም የሻ ሲንፉን 95 በመቶ ያህሉን ዕጢ ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ከአንገታቸው ላይ አስወገዱላቸው፡፡

4CBF506E00000578-5786143-image-a-14_1527671746483.jpg

ዶክተር ዶንግ በህክምና ህይወታቸው በዚህ መጠን ትልቅ ዕጢ አጋጥሟቸው እንደማያውቅ በግርምት ተናግረዋል፡፡

ዕጢው ሊፖማ በመባል የሚጠራ ሲሆን፥ በየትኛውም የሰውነታችን ክፍል ውስጥ ሊወጣ ይችላል እንዲሁም አብዛኛውን ጊዜ ህመም አልባ ነው ተብሏል፡፡

4CBF518D00000578-5786143-image-a-13_1527671740644.jpg

 

ምንጭ፦ዴይሊይሜል

በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram