fbpx

ትንሽ ሰው ትንሽ ነው፤ አንሶ ያሳንሳል

“ትንሽ ሰው ትንሽ ነው፤ አንሶ ያሳንሳል” …
(ሊያውቁት የሚገባ!)

ትንሽ ከፊት ሲሆን አገር ያሳንሳል፡፡ (ፋሲል ደሞዜ)

በኩር ጋዜጣ ነጻ አስተያየት በሚሰጥበት አምዱ ይሄን አስተያየት ይዟል፡፡ ሙሉውን አንብቧት !

-አደባባይ የወጣነው ላለፉት 27 ዓመታት በዘር፣ በጎሳና በጎጥ እየለያዩ ሲያጨፉጭፉን፤ አንጡራ ሀብታችንን እየዘረፉ በድህነት ሲያቆራምዱን፣ ጠባብና ትምክህተኛ የሚሉ ተለጣፊ ስያሜዎችን እያደሉ ስነልቦናችንን ሲሸረሽሩ፤ ህፃን፣ እናት፣ ነፍሰጡርና አረጋዊያንን ሳይቀር በአደባባይ ሲረሽኑ፣ ዜጎችን በጨለማ እስር ቤቶች ሲደበድቡ፣ ብልት ሲያኮላሹ፣ ጥፍር ሲነቅሉ፡ በቫይረስ ሲበክሉ፣ ይህንን ሁሉ በደል በንፁሃን ላይ ሲፈፅሙ የኖሩ የቀን ጅቦችን ፍቅር ይበልጣል ብለን ስንታገስ ቦንብ የተወረወረብን ለምን ይሆን??

– ትናንት የዲሞክራሲ ጥያቄ አንስተው ባዶ እጃቸውን አደባባይ በመውጣታቸው በጥይት የጨፈጨፋችሃቸው የአማራና ኦሮሞ ወጣቶች ደም ሳይደርቅ፣ የሆነውን እንዳልሆነ ትተን ይቅርታን መምረጣችን ፍርሃት የወለደው አማራጭ መስሎ ታያችሁ ይሆን??

-ደጃችን ላይ ሞፈር ስትቆርጡ፣ ጀነሬተሮች፣ ትራንስፎርመር፣ ክሬሸር፣ ፓፕና ማሽነሪ ሁሉ ወደ አንድ ጎጥ ስታግዙ፤ አየር መንገድን፣ ጉምሩክን፣ መከላከያውን፣ ኢምግሬሽን፣ ባንክና ኢንሹራንሱን በአንድ ብሔር ተቆጣጥራችሁ ወርቃችንን በባሌስትራ ስትቀይሩ ችለን ማለፋችን በናንተ ቤት እንደፍራቻ ተቆጥሮ ነው??

-ስማችሁ ፎርጅድ የትምህርት ማስረጃችሁ ፎርጅድ፣ ሀብታችሁ ፎርጅድ መሆኑን እያወቅን እናንተ አለቃ እኛ ምንዝር የሆነው ፈሪ ሆነን ይመስላችኋል???
-ባህርዳር ላይ የአልማን ጽ/ቤት ዘርፋችሁ ያቀጠላችሁት መሆኑን የማናውቅ ይመስላችኋል??

– የፓፒረስ ሆቴል ባለቤት አቶ ጠብቀውን፣ የብሉ ናይል አቫንቲ ሪዞርት ባለቤት አቶ መኮነን ገበየሁን፣ የደስ ጥጥ መዳመጫ ባለቤት አቶ ደሳለኝን ጨምሮ በርካታ የአማራ ባለሃብቶችን የገደላቸው ማን ነው? ሀብታቸውንስ የወረሰው ማን ሆነና??

-የኤሌክትሪክ ሀይል ምንጮቹ የእኛዎቹ ዓባይ፣ ተከዜ፣ በለስና ጊቤ ሆነው ሳለ እኛ በኩራዝ እየተጨናበስን እናንተ አመቱን ሙሉ በኤሌክትሪክ ብርሃን ስታብረቀርቁ አለመቃወማችን ያስንቃል እንዴ??

-ጥምቀት በወልዲያ፣ እሬቻን በኦሮሚያ ስታደፈርሱ በዩኒስኮ የተመዘገበችውን የጎንደር ከተማ በእሳት ስታጋዩ መታገሳችን ፍርሃት አይደለም፡፡ ሁሉም ትዕግስት ለኢትዮጵያ ሲባል እንጂ እንደእናንተ ተግባርማ አንድም ቀን ይከብዳል፡፡

ትዕግስትም ፍርሃት አለመሆኑን ተረድታችሁ ከእኩይ ተግባራችሁ ልትታቀቡ ይገባል እንላለን፡፡ እኔ ከሞት ሰርዶ አይብቀል እንዳለችው አህያ እኛ ካልገዛናችሁ አትኖሯትም የምትሉትን የጅል ፈሊጥ እርሱት!!!

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram