fbpx

ትናንት በኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ 27ኛ ሳምንት 4 ጨዋታዎች ተካሂደዋል

በአዲስ አበባ ስቴድየም ወልድያ ስፖርት ክለብ በመሪዉ ጅማ አባ ጅፋር 2 ለ 0 ተሸንፏል፡፡

ወልዲያ ትናንት መሸነፉን ተከትሎ 3 የዉድድር ጨዋታዎች እየቀሩ መዉረዱን አረጋግጧል፡፡

ፋሲል ከነማ ጎንደር ላይ ሲዳማ ቡናን አስተናግዶ 2ለ1 አሸንፏል፡፡

ፋሲል ከ 6 ተከታታይ ጨዋታዎች በኋላ ነዉ ወደ አሸናፊነት የተመለሰዉ፡፡
ለፋሲል ከተማ ሁለቱን ግቦች ኤፍሬም አለሙና ራምኬ ሎክ አስቆጥረዋል፡፡
ሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስም ደደቢትን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ጅማ አባጅፋር በ48 ነጥብ ፕሪሜር ሊጉን በበላይነት ይመራል፤ ጊዮርጊስም በተመሳሳይ 48 ነጥብ ይዞ በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጧል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና 43 ነጥብ ይዞ በፕሪሜር ሊጉ 3ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ክለብ ነዉ፡፡
ኢትዮ ኤሌክትሪክ፤አርባ ምንጭና ወልዲያ ወራጅ ቀጠና ተቀምጠዋል፡፡
ዛሬ ቀን 09፡00 ሰዓት መቀሌ ከመከላከያ ፤ አዳማ ከተማ ከአርባ ምንጭ የሚገናኙ ይሆናል፡፡

በባዘዘው መኮንን –  አብመድ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram