fbpx

ቴምርና የጤና ጠቀሜታዎቹ

ቴምር በተለይም በረመዳን ጾም ወቅት በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በስፋት ይዘወተራል።

ይህ ፍሬ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት የሚነገርለት ቴምር፥ በርከት ያሉ ቫይታሚኖች እና ማዕድናትን በመያዙ ለሰውነት እጅጉን ጠቃሚ መሆኑ ነው የሚነገርለት።

ሀይል ሰጪ፣ ፋይበር፣ ካልሺየም፣ አይረን፣ ፎስፈረስ፣ ሶዲየም፣ ፖታሺየም፣ ማግኒዢየም እና ዚንክ የመሳሰሉ ማዕድናት በቴምር ውስጥ የሚገኙ በመሆኑ ቴምርን ለጤና ጠቃሚ ያደርጉታል።

ከቴምር ጠቀሜታዎች ጥቂቶቹም፦

የሆድ ድርቀትን ለመከላከል፦ ቴምር የማለስለስ ባህሪ ስላለው ምግብ በአንጀታችን ውስጥ በቀላሉ እንዲዘዋወር በማድረግ የሆድ ድርቀትን ለመከላከል ይረዳል።

ለዚህም ይረዳ ዘንድ ቴምሩን በውሃ ውስጥ ዘፍዝፎ በማሳደር ጠዋት ላይ መመገብ ይመከራል።

ለአጥንት ጤንነትና ጥንካሬ፦ በቴምር ውስጥ የሚገኙ ማዕድናት ለአጥንት ጥንካሬ እና ጤንነት እጅጉን ጠቃሚ እንደሆኑ ይነገራል።

ቴምር እንደ ሴሊኒየም ማንጋነዝ፣ ኮፐር እና ማግኒዢየም ማዕድናትን በውስጡ በመያዙም ለአጥንት ጤናማ እድገት እና ጥንካሬ ጠቃሚ ነው።

ለደም ማነስ፦ ቴምር በውስጡ በያዘው ከፍተኛ የምግብ ማዕድናት ንጥረ ነገሮች ክምችት የደም ማነስ ችግር ላለባቸው ሰዎች እጅጉን ጠቃሚ ነው።

አለርጂን ለመከላከል፦ ቴምርን ከሌሎች ለየት የሚያደርገው አለርጂን ለመከላከል የሚረዳው ሰልፈርን በውስጡ መያዙ ነው።

ቴምርን አዘውትሮ መመገብ ለተለያዩ አይነት አለርጂዎች የመጋለጥ እድልን እጅጉን እንዲቀንስ እንደሚያደርገው ይነገርለታል።

ለነርቭ ጤንነት፦ በቴምር ውስጥ የሚገኙት ቪታሚኖች የተስተካከለ እና ጤናማ የነርቭ ስርዓት እንዲኖር ስለሚያደርጉ ለጤና ጠቃሚ ያደርገዋል።

ለልብ ጤንነት፦ ቴምር ለልብ ጤንነት በርካታ ጠቀሜታዎች ስላሉት ተመራጭ ያደርገዋል።

ቴምር የልብ ጤንነትን ይጎዳል የሚባለውን የኮሌሊስቴሮል መጠን የመቀነስ አቅም ስላለው ለድንገተኛ የልብ ህመም የመጋለጥ እድልን በመቀነስ ለልብ ጤንነት ጠቀሜታ አለው።

ለስንፈተ ወሲብ፦ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ቴምር በውስጡ በያዘው ንጥረ ነገር አማካኝነት የሰዎችን የወሲብ ፍላጎት ከፍ እንዲል እና የወሲብ ፍራቻ ላለባቸው ሰዎች ድፍረትን እንዲያገኙ በማድረግ ስንፈተ ወሲብን ለመከላከል ይረዳል።

በእርግዝና እና ወሊድ ወቅት ተመራጭ ምግብ ነው

ቴምር በእርግዝና ወቅት ለጽንሱ ጤንነት ብሎም በወሊድ ጊዜ ምጥ አስቸጋሪ እንዳይሆንና የተሻለ የማማጥ አቅም እንዲኖር ያስችላል።

ለአዕምሮ ጤንነት፦ ጥናቶች በቴምር የሚገኘው ቫይታሚን ቢ6 የተሻለ የአዕምሮ ተግባራት እንዲኖርና ሰዎች በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ማገዙን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ naturalsociety.com

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram