ተመድ ተጨማሪ ሰላም አስከባሪ ሃይል ወደ ደቡብ ሱዳን ላከ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን ተልዕኮ በሀገሪቱ ካለው የእርስ በእርስ ጦርነት ንጹሃን ዜጎችን ለመጠበቅ ተጨማሪ 150 ሰላም አስከባሪ ጦር ወደ ስፍራው መላኩን አስታወቀ፡፡

ጦሩ በተለይ ግጭት ወደ በረታባት እና በነዳጅ ሀብቷ በበለጸገችው ዩኒቲ ግዛት እንደሚሰማራ ታውቋል፡፡

በዚህ ግዛት ባለፈው ሳምንት ብቻ 30 ቤቶች ጥቃት የደረሰባቸው ሲሆን በዚህ ግጭት ብዙ ሰዎችም ለህልፈት ተዳርገዋል ተብሏል፡፡

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ሃይሎች በሀገሪቱ ሰላም እንዲያወርዱ ተደጋጋሚ ስምምነት ቢፈፅሙም ተግባራዊ ማድርግ አለመቻላቸው ተገልጿል፡፡

ላለፉት 5 ዓመታት በደቡብ ሱዳን ባለው የእርስ በእርስ ጦርነት ከ1.7 ሚሊዮን በላይ ዜጎች አካባቢያቸውን ለቀው ለመሸሽ ተገደዋል፡፡

ምንጭ፡- የሮይተርስ

Share your thoughts on this post