ባለ ሁለት ገፅ ስክሪን ላፕቶፕ ይፋ ተደረገ

ኢንቴል ኩባንያ ከዚህ ቀደም ከነበረውና ከተለመደው ላፕቶፕ በተለየ ሁኔታ ኪቦርድን በማስቀረት ባለ ሁለት ገፅ ስክሪን አዘጋጅቶ ይፋ አድርጓል።

ይህ ቀላል ላፕቶፕ ታጥፈው የሚገጠሙት ሁለቱም አካላቶቹ ስክሪን ሲሆኑ፥ የወረቀት ማስታወሻን የመሰለ የኤሌክትሮኒክ የተገጠመላቸው መሆኑ ተነግሯል።

አዲሱ ባለ ጥምር ስክሪን ላፕቶፕ ያለው የማስታወሻ ደብተር መሳይ አካል በጣም ስስ እና ከጥጥ ከሚዘጋጀው ሞሌስኪኔ ማስታወሻ ደብተር ጋር ይመሳሰላል ተብሏል።screan_3.jpg

የዚህን ባለ ጥምር ስክሪን ላፕቶፕ አንዱን ስክሪን ኪቦርድ አድርጎ መጠቀም የሚቻል ሲሆን በዚህም ኪቦርዱ መስታወት ይሆንል።

ባለተጣታፊ ስክሪን ላፕቶፕ ሰዎች ከባድ ስራን ስብሰባ ላይ በሚሆኑበት ወቅት በራሱ ጊዜ ቀን መቁጠሪያን በማየት መስራት እንዲቻል እድልን ይፈጥራል።

ከዚህ ባለፈ ባትሪን በአግባቡ መጠቀም የሚያስችል እንደሆነ ነው የተነገረው።

ይህ ምርትም በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ጀምሮ ለገበያ እንደሚቀርብ ታውቋል።

ምንጭ፦ ዘቨርጅና www.cnet.com

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram