fbpx

በ47 ዓመታቸው የ20 ዓመት ሞዴል የሚመስሉት ጃፓናዊት

ሪሳ ሂራኮ የተባሉት የ47 አመት አዛውንት ሞዴል በእስያ ሀገራት ወጣትነት በመላበስ ተወዳዳሪ እንዳልተገኘላቸው ኦዲቲ ሴንትራል ዶት ኮም በዘገባው አስፍሯል።

ወይዘሮዋ ለተመልካቾቻቸው በ20ዎች እድሜያ ክልል ካሉ ወጣት ሴቶች ሚመደቡ ሲሆን፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ 222 ሺህ ያህል የኢንስታግራም ተከታዮች እንዳሏቸውም ተገልጿል።

በሞዴል እንዱስትሪው እና በስራ ፈጠራ ውጤታማ የሆኑት ሪሳ ሂራኮ በጃፓን ታዋቂ የሆኑት ኢዛኩ ዮሸዳ የተባሉት የፊልም ተዋናይ ባለቤት እና ትልቅ እውቅና ያላቸው ሴት መሆናቸውንም ነው ዘገባው የሚያስርዳው።

የወይዘሮዋ የቆዳ ጤና አጠባበቅ፣ አመጋገብ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የጤና ሁኔታ ይህን ጸጋ ሳያጎናጽፋቸው እንዳልቀረ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።

ወይዘሮዋ ውጫዊ ውበትና ወጣትነት ብቻ ሳይሆን ውስጣዊ ጥንካሬንም የታደሉ እንደሆነ ነው የተገለጸው።

በዚህም ወይዘሮዋ በእስያ ሃገራት በ47 ዓመታቸው የወጣትነት ቁመናን በመላበስ ተወዳዳሪ ያልተገኘላቸው መሆኑን ነው ኦዲቲ ሴንትራል በዘገባው ያስነበበው።

ምንጭ፦odditycentral.com

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram