fbpx

በፕሪምየር ሊጉ ጅማ አባ ጅፋር ደደቢትን አሸነፈ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 28ኛ ሳምንት በተለያ ጨዋታዎች በዛሬው ተካሄዷል።

ደደቢትን ጅማ ላይ ያስተናገደው ጅማ አባ ጅፋር 3 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን ማረጋገጥ ችሏል።

በጨዋታው ጅማ አባ ጅፋርን አሸናፊ ያደረጉ ግቦች ኦኪ አፎላቢ በ17ኛው፣ 90ኛው ደቂቃ እና ተመስገን ገ/ኪዳን 51ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥረዋል።

በሌላ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪከ ፋሲል ከነማን አስተናግዶ 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ኤሌክትሪክን አሸናፊ ያደረጉ ግቦች አዲስ ነጋሽ በ27፣ በ54ኛው ደቂቃ ፣ዲዲዮ በ44ኛው ደቂቃ እና አልሀሰን ካሉሻ በ61ኛው ደቂቃ ሲያስቆጥሩ ፋሲል ከነማን ከመሸነፍ ያላዳነችውን ግብ ሀሚስ ኪዞ በ39ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።

ሲዳማ ቡና የዋንጫ ተፎካካሪ የሆነውን መቐለ ከተማን አስተናግዶ 2 ለ 1 አሸንፏል።

በዚህ ጨዋታ አዲስ ግደይ ሲዳማ ቡናን አሸናፊ ያደረጉ ሁለት ግቦች በ50ኛው እና 75ኛው ደቂቃ ሲያስቆጥር የመቐለን ብቸኛው ግብ ፉሴይኒ ኑህ አስቆጥሯል።

በተመሳሳይ መከላከያ ወልዲያን አስታናግዶ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ምንይሉ ወንድሙ እና ፍፁም ገ/ማሪያም በ12ኛው እና በ28ኛው ደቂቃ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ሀዋሳ ከተማ ከአርባ ምንጭ ያደረጉት የደቡብ ደርቢ ጨዋታ 0 ለ 0በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

በሌላኛው ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ ፕሪንስ ሰቨሪንሆ በ51ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ አደማ ከተማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ፕሪምየር ሊጉን ጀማ አባ ጅፋር በ51 ነጥብና በ19 የግብ ክፍያ እየመራ ይገኛል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram