fbpx

በፕሪምየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና ከደደቢት ይገናኛሉ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 24ኛ ሳምንት ጨዋታ ፋሲል ከነማ ድሬደዋን የሚያስተናግድ ሲሆን፥ አዲስ አበባ ላይ በሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ከደደቢት ይገናኛሉ።

በሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘውን ደደቢትን በአዲስ አበባ ስታድየም ያስተናግዳል።

ሁለቱ ቡድኖች 17 ጊዜ በሊጉ ተገናኝተው ደደቢት 10 ጊዜ በማሸነፍ ቅድሚያውን ሲይዝ ኢትዮጵያ ቡና 6 ጊዜ ያሸነፈ ሲሆን፥ አንድ ጊዜ ብቻ አቻ ተለያይተዋል።

በፕሪምየር ሊጉ ቡናዎች በ36 ነጥብ አራተኛ ደረጃ የሚገኝ ሲሆን፥ ከሊጉ መሪነት እየወረደ የመጣው ደደቢት በ33 ነጥብ ስድሰተኛ ደረጃ ላይ ነው።

በትናትናው ዕለት ጎንደር ላይ በነበረው ዝናብ ምክንያት ሳይካሄድ የቀረው ፋሲል ከነማን ከድሬደዋ ከተማ የሚያገናኘው ጨዋታ ዛሬ 4 ሰዓት ላይ በአፄ ፋሲለደስ ስታድየም የሚካሄድ ይሆናል።

ፋሲል ከነማ በደረጃ ሰንጠረዥ በ33 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ፥ ድሬደዋ ከተማ በ25 ነጥብ በ13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ሊጉን መቐለ ከተማ በ42 ነጥብ ሲመራ ጅማ አባጅፋር እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በእኩል 41 ነጥብ በጎል ክፍያ ተበላልጠው 2ኛ እና 3ኛ ሆነው ይከተላሉ።

 

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram