በፕሪሚየር ሊጉ መቐለ ከተማ ሲያሸንፍ ጅማ አባ ጅፋር ነጥብ ተጋርቷል

የ24ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል።

አዲስ አበባ ላይ የተደረገው የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ወላይታ ዲቻ ጨዋታ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ወልዋሎን ከጅማ አባ ጅፋር ያገናኘው ጨዋታ ደግሞ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ፍጻሜውን አግኝቷል።

ይርጋለም ላይ አዳማ ከተማን ያስተናገደው ሲዳማ ቡና ደግሞ 1 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።

መቐለ ላይ ደግሞ መቐለ ከተማ ከሃዋሳ ከተማ ተጫውተው ባለሜዳው መቐለ 1 ለ 0 አሸንፏል።

ወልድያን ያስተናገደው አርባ ምንጭ ከተማ 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ የጎል ልዩነት አሸናፊ ሆኗል።

ጎንደር ላይ ፋሲል ከነማ ከድሬዳዋ ከተማ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ጎንደር ላይ በጣለው ዝናብ ሜዳው ማጫወት ስለማይችል ጨዋታው ለነገ ረፋድ ተዛውሯል።

ሊጉን መቐለ ከተማ በ42 ነጥብ ሲመራ ጅማ አባጅፋር በ41 እንዲሁም አንድ ቀሪ ጨዋታ ያለው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ40 ነጥብ ይከተላሉ።

Share your thoughts on this post

Advertisements
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram