fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

በጠርሙስ ውስጥ ተደርጎ ከ132 ዓመታት በፊት የተላከ መልዕክት በአውስትራሊያ የባህር ዳርቻ ተገኘ

 የአውስትራሊያ ባለሙያዎች ከ132 ዓመታት በፊት በጠርሙስ ውስጥ ተደርጎ ለባህር ሀይል የተላከ መልዕክት በሀገሪቱ የባህር ዳርቻ ማግኘታቸውን አስታወቁ።

ቶንያ ኢልማን የተሰኙ አንድ ባለሙያ በአውስትራሊያ ምዕራባዊ አቅጣጫ በሚገኝ የባህር ዳርቻ ባለ አሸዋማ ስፍራ በመጓዝ ላይ እያሉ ነበር ጠርሙሱን ያገኙት።

የቶንያ ባለቤት ኪም ኢልማን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ እንደዘገበው፥ ጠርሙሱን ሲያገኙት ወረቀት እንዳለው ብያውቁም ወደቤታቸው ወስደው አድርቀው እስኪያዩት ድረስ መልእክት ይኖረዋል የሚል እምነት አልነበራቸውም።

ባልና ሚስቱ ከባለሙያዎች ዘንድ ባገኙት ማብራርያ በአውሮፓውያኑ ሰኔ ወር 1886 ከአንድ የጀርመን መርከብ ለባህር ሀይል የተላከ ትክክለኛ መልዕክት እንደነበር አረጋግጠዋል።

በዚህም በ19ኛው ከፍለ ዘመን በጠርሙስ ውስጥ ተደርጎ የተላከው ደብዳቤ ሳይነበብ ለ132 ዓመታት ቆይቷል።

ከዚህ በፊት በጠርሙስ ተደርጎ ከ108 ዓመታት በፊት የተላከው ደብዳቤ በአለም ድንቃድንቅ መዝገብ ውስጥ ሰፍሮ እንደነበር ይታወሳል።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram