በግሪክ በተቀሰቀሰ የእሳት አደጋ ቢያንስ 50 ያህል ዜጎች ሳይሞቱ እንዳልቀሩ ታውቋል።
የእሳት አደጋው በ10 ዓመታት ውስጥ በአካባቢው ከተከሰቱት ተመሰሳይ አደጋዎች ከፍተኛና እስከፊው ነው ተብሏል።
አደጋው በግሪክ አቴንስ ከተማ አቅራቢያ በምተገኘው ማቲ በተባለች መንደር የተቀሰቀሰ ሲሆን፥ የ50 ያህል ሰዎች ህይወት ማለፉ እና 26 ያህሉ አሁንም በዚሁ አካባቢ በእሳት ከተያያዘ ህንጻ ያለመውጣታቸው ነው የተገለጸው።
የእሳት አደጋው በከተማዋ የባህር ዳርቻ አካባቢ የተከሰተ ሲሆን፥ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በሂሊኮፕተርና በጀልባ በመታገዝ ነዋሪዎቹን ከአደጋው ለማትረፍ እየተረባረቡ ነው ተብሏል።
የከተማ አስተዳደሩ የዓለም አቀፍ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ማስታወቁም ነው የተገለጸው።
በመቶዎች የሚቆጠሩ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞቹ እሳቱን ለመከላከል እየተረባረቡ ሲሆን፥ ነዋሪዎቹም ከእሳቱ ለማምለጥ ቤታቸውን ለቀው እየወጡ መሆኑም ተመላክቷል።
በቃጠሎው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ተለያዩ ሆስፒታሎች አየተወሰዱ ሲሆን፥ 104 ያህል ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል ተብሏል።
ጉዳቱ ከደረሰባቸው መካከል 11 ያህሉ የከፋ ደረጃ ላይ የደረሱ ሲሆን፥ ከጉዳተኞ መካከል 16ቱ ህፃናት ናቸው ተብሏል ።
ምንጭ ፦ bbc.com
የተተረጎመው፦ እንቻለው ታደሰ
Share your thoughts on this post