fbpx

በግል ጤና ተቋማት ያለውን ከፍተኛ የወሊድ አገልግሎት ክፍያ ለመቆጣጠር እየተሰራ ነው

በግል ጤና ተቋማት ያለውን ከፍተኛ የወሊድ አገልግሎት ክፍያ ለመቆጣጠር ጤና ጣቢያዎችን የማጠናከር ስራ እየተሰራ ነው።

በመዲናዋ የግል የህክምና ተቋማት ለቀዶ ህክምና የወሊድ አገልግሎት ከ10 ሺህ እስከ 15 ሺህ ብር ሲያስከፍሉ ይስተዋላል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የፈውስና ተሀድሶ ህክምና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አባስ ሀሰን፥ ችግሩን ለመቆጣጠር ጤና ጣቢያዎችን በሰው ሀይል እና በመሳሪያ የማደራጀት ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

ይህም በጤና ጣቢያዎች የኦፕሬሽን ወሊድ አገልግሎት መስጠት ያስችላል ያሉት ዳይሬክተሩ፤ በአሁኑ ወቅትም አገልግሎቱን ጃን ሜዳ እና ኮልፌ ጣና ጣቢያዎች መጀመራቸውን ጠቅሰዋል።

ከዚህ በተጨማሪም አጠቃላይ የጤና ጣቢያዎችን አገልግሎት ለማሻሻል በአፈጻጸማቸዉ የተሻለ ደረጃ ላይ ያሉ የመንግስት ሆስፒታሎች ፤ጤና ጣቢያዎቹን እንዲያበቁ እና እንዲደግፉ የሚያስችል አሰራር ተዘርግቷል ነዉ ያሉት።

በቤተልሄም ጥጋቡ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram