fbpx

በጋላፊ ቅርንጫፍ ባለው የሲስተም እና መብራት ችግር ለእንግልት መዳራጋቸውን ሹፌሮች ገለፁ

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የጋላፊ ቅርንጫፍ ባለው የሲስተም እና መብራት ችግር ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረጉ መሆኑን ሽፌሮች ገለፁ።

ይህን ቅሬታ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያቀረቡት ሹፌሮች በጁቡቲ መስመር አስር አመት እና ከዛም የሰሩ ናቸው።

ሹፌሮቹ ባለፉት ሶስት እና አራት ዓመታት በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የጋላፊ ቅርንጫፍ እየጋጠማቸው ያለው ችግር ስራ እና ህይወታቸውን አስቸጋሪ እንዳደረገው ይናገራሉ።

በቅርንጫፍ ተደጋጋሚ በሚከሰተው የመብራት እና የሲስተም መቆራረጥ ረጂም ወረፋ የሚፈጠር በመሆኑ በአካባቢው ካለው ሙቀት እና ሃሩር እስከ ሶስት ቀን ወረፋ ለመጠበቅ መገዳቸውን ተናግረዋል።

ሹፌሮቹ የስራዎችን ለመስራት በቂ የሰው ሃይል እንደማይመደብና ሙያውን አውቆ በሚፈለገው ፍጥነት የሚጠበቅበን አገልግሎት ለመስጠት ክፍተት እንዳለባቸው ነው የሚገልፁት።

በመስመሩ ካለው ከፍተኛ የተሽከርካሪዎች ፍሰት እና የኢኮኖሚው አስተዋፅኦ አሰራሩ ዘመናዊ እና ፈጣን መሆን የነበረበት ቢሆንም ተግባራዊ አልተደረገም ብለዋል።።

በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ በሚስተዋለው ችግር ሾፌሮቹ የተረከቡትን ንብረት በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ እና መስፈርት ለማድረስ እንደተቸገሩም ይገልፃሉ።

በዚህ ችግር ምክንያት በቂ ምግብ እና ውሃ በማይገኝበት ሞቃታማና ሃሩሩማ አካባቢ እስከ ሶስት ቀናት መቆየታቸውን በቅሬታ መልኩ ለቅርጫፉ ሲያቀርቡም ተጨማሪ እንግልት ከሰራተኞች እንደሚደርስባቸው ነው ሹፌሮቹ ያስታወቁት።

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የጋላፊ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋየ አየለ፥ ከሾፌሮቹ በኩል የቀረበው ቅሬታ የተጋነነ መሆኑን ነው የተናገሩት።

ስራ እስኪያጁ፥ ባለፈው ሳምንት በጎርፍ ምክንያት ሹፌሮቹ ያነሱት ቅሬታ የተፈጠረ ቢሆንም የሃይል ችግሩ በሁለት ቀናት ውስጥ መፍታት እንደተቻለ ተናግረዋል።

በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ወረፋዎች የሚፈጠሩ ቢሆንም በሹፌሮቹ በኩል የሚነሳው ቅሬታ በተባለው ልክ አለመሆኑን እና የተጋነነ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ከዚህ በፊት ተፈጥሮ የነበረው የመብራት ችግር የተፈታ ሲሆን፥ የተፈጠረውን የሲስተም ችግር ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ስራ አስኪያጁ አስታውቀዋል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram