fbpx

በጃፓን የጣለው ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው አደጋ የሟቾች ቅጥር 199 ደረሰ

በጃፓን የጣለው ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው አደጋ የሟቾች ቅጥር 199 መድረሱ  ተገልጿል።

በሀገሪቱ ከባድ ዝናብ ባስከተለው አደጋ የ199 ያህል ዜጎች ህይወት መጥፋቱንና ቢያንስ 10 ሺህ ያህል ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸው እንዲፈናቀሉ ማድረጉን ሲጂቲኤን የጃፓን መንግስት ቃል አቀባይን ዋቢ አድረጎ ዘግቧል።

ከባዱ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ሳቢያ በርካታ ዜጎች የደረሱበት ያልታወቀ ሲሆን፥ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የማፈላለግ ስራ ላይ መሆናቸውም ታውቋል።

በሃገሪቱ በዝናብና በአየር ንብረት ሳቢያ ባለፉት 3 አስርት አመታት ከተከሰቱት አደጋዎች ይህ ከባዱ መሆኑንም ነው ዘገባው የሚያስረዳው።

 

 

ምንጭ፦ cgtn.com

የተተረጎመው፦ በእንቻለው ታደሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram