fbpx

በጃፓን በተከሰተው ጎርፍ ምክንያት ጣሪያ ላይ የሰነበተችው ፈረስ

ባለፈው አርብ በጃፓን ከ170 ሰው በላይ ለህልፈት የዳረገ ጎርፍ መከሰቱ ይታወሳል፡፡

ጃፓን መጠኑ ከፍ ያለ ዝናብ እያሰተናገደች ትገኛለች በዚህም በርካታ ሰዎች ከቀዬያቸው ተፈናቅለዋል፡፡

ከሰዎች በተጨማሪ ሊፍ በመባል የምትጠራው ፈረስም የት እንደተሰወረች አልታወቀም ነበር፡፡

ሊፍ በጎርፍ ሳትወሰድ አልቀረችም የሚሉ ድምጾችም ተስተጋብተው ነበር በመጨረሻም የሊፍ ጠበቂ የሆኑት 49 ዓመቱ ማሪ ታኒሞቶ

ምናልባትም ከጎርፍ አደጋው በመዋኘት ልታመልጥ እንደምትችል መላምታቸውን አስቀመጡ፡፡

የጎርፉ መቀነስ ተከትሎ ታዲያ ማሪ ታኒሞቶ ፍለጋቸውን በየተራራውና ጉብታው ላይ አደረጉ፡፡

በመጨረሻም የማሪ መላምት መና ሆኖ አልቀረም ሊፍ በአንድ ግለሰብ ቤት ጣሪያ ላይ ቆማ ተገኘች፡፡

የተለያዩ ግለሰቦች በሊፍ መሞት እርግጠኛ ሆነው ነበር ነገርግን በመልካም ጤንነት ላይ ሆና ጣሪያ ላይ መገኘቷ ግርምትን ፈጥሮባቸዋል፡፡

ጃፓናውያንም የሊፍን መገኘት ተከትሎ እየጎበኙዋት ይገኛሉ ተብሏል፡፡

57eebc7b4ccb477e07b7e25f38bfe205.jpg

 

 

ምንጭ፦ፎክስ ኒውስ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram