fbpx

በዴሞክራቲክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቮላ ቫይረስ ወደ ምባንዳካ ከተማ ተዛመተ

በቅርብ ጊዜ በዴሞከራቲክ ጎንጎ የገጠር አካባቢዎች የተከሰተው የኢቮላ ቫይረስ ስርጭት ወደ ዴሞክራቲክ ኮንጎዋ ምባንዳካ ከተማ መዛመቱ ተገልጿል።

የቫይረሱ በፍጥነት ወደ ከተሞቹ እየተስፋፋ መምጣት በአካባቢው ውጥረት እንዲነግስ ማድረጉ ነው የተገለጸው።

የ1ሚሊየን ያህል ዜጎች መቀመጫ በሆነችው ምባንዳካ ከተማ ቫይረሱ መከሰቱን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር ኦሊይ ካሌንጋ ያረጋገጡ ሲሆን፥ ከተማዋ ከዚህ ወር በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ቫይረሱ ከተከሰተበት አከባቢ 80 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ እንደምትገኝም ነው የተገለጸው።

በዚህም 43 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውና 23 ያህል ሰዎች ህይዎት እንዳለፈም ነው ዘገባው የሚያመላክተው።

በዴሞክራቲክ ሪፓፕሊክ ኮንኮ ኢኮዌቶር ግዛት በ3 የጤና ጣቢያዎች በበሽታው የተጠረጠሩ ህሙማን መመዝገባቸው ታውቋል።

ይሁን እንጂ ተጠርጣሪዎቹ የተመዘገቡት ለትራንስፖርት ቅርበት ባለቸውና በቀላሉ ሊደረስባቸው በሚችሉ አካባቢዎች ብቻ ነው ተብሏል።

ምባንዳካ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሃገሪቱ ዋና መዲና ኬኒሻሳ የምታገናኝ ሲሆን፥ የትራንስፖርት አገልግልት በሚሰጠው የጎንጎ ወንዝ አካባቢ የምትገኝ በመሆኗ በሽታው በቀላሉ ወደ ኮንጎ ብራዛቪል፣ ሴንትራል አፍሪካ ሪፐፕሊክና ኬኒሻሳ ከተማ በቀላሉ ሊስፋፋ እንደሚችል ተጠቁሟል።

በአለም ጤና ድርጅት የአደጋ ዝግጁነትና ምላሽ ምክትል ዳይሬክተር ጀኔራል ፒተር ሰላማ በሽታው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከተማ ውስጥ መከሰቱ በፍጥነት እንዲዛመት የሚያደርገው ሲሆን፥ በቀላሉ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ የሚደረገው መሆኑን አስርድተዋል።

ክስተቱ አሁን ባለበት ደረጃ እንዲቆም ለማድረግ መረባረብ የሚያስፈልግ መሆኑን ነው ፒተር ሰላማ የሚናገሩት።

በዚህም የዓም ጤና ድርጅት 4ሺህ ዶዝ የክትባት መድሃኒት ወደ ሀገሪቱ ሰሞኑን መላኩን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ ወደፊትም የሚደርስ የክትባት መድሀኒት መኖሩን አስረድተዋል።

የክትባት መድሃኒቱ በሙከራ ደረጃ ላይ ቢሆንም ተስፋ ሰጭ ውጤቶች የተመዘገቡበት እንደሆነ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ መድሃኒቱን ከቦታ ቦታ ለመጓጓዝና ሳይበላሽ አገልግሎት ላይ ለማዋል የሀይል አቅርቦት በሌለበትና የመሰረተ ልማት ባልተሟላባችው አካባቢ ለማድረስ አስቸገሪ መሆኑን ነው የተገለጸው።

በሽታው በደምና በሰውነት ፈሳሽ በቀላሉ የሚተላለፍና ገዳይ ሲሆን፥ በመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች ከጉንፋን ጋር ተመሳሳይ ምልክቶች እንዳሉት ተመላክቷል።

 

ምንጭ፦ bbc.com

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram