fbpx

በደምቢዶሎ የተገኙት ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የደምብዶሎ ዩኒቨርሲቲን ዛሬ መርቀው ከፈቱ

ዶ/ር አብይ አህመድ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ከዞኑ ከተወከሉ የህብረተሰብ ክፍሎችና ለደምቢዶሎ ከተማ ነዋሪዎችም ንግግር አድርገዋል፡፡

ዶ/ር አብይ በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የአከባቢው ህዝብ በእውቀት ይታወቃል፣ የዚህ አከባቢ ህዝብ ዘመናዊ ትምህርትን በመጀመር ለዚህ አገር ህዝብ ትምህርት ምን እንደሆነ፣ መማር ምን ለውጥ ማስገኘት እንደሚችል ማሳየት የቻለ ህዝብ ነው ብለዋል፡፡

ዛሬ የተባባሩት መንግስታት ድርጅት ከሄዳችሁ 10 የዚህ አገር ሰው ያለ እንደሆነ ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ ከደምቢዶሎ ቤዝ የወጡ እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም፣ የደምቦዶሎ ቤዝ ለዚህ አገር ትምህርት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፣ ዛሬ የሚመረቀው ዩኒቨርሲቲም ከቤዝ ጋር በመሆን ጥናትና ምርምር በመስራት አገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲትሆን ለማድረግ የበኩሉን ሚና እንደምጫወት እምነት አለኝ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

“ጠንክረን ከሰራን በ5 እና 10 ዓመታት ውስጥ ለውጥ ማምጣት እንችላለን፣ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ዩኒቨርሲቲዎቻችን የሌሎች አገራት ተማሪዎች መጥተው የሚማሩበት ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ እንደምሆኑ ተስፋ አለኝ፣ ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ ተማሪዎችን አንድ ላይ ማስተማር እንደ ትልቅ እውቀት በሚታይበት በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ብሔር ብሔረሰብ ተማሪዎችን አቅፎ ማስተማር ለእኛ ትልቅ ክብር ነው፣ ስለዚህ እዚህ አከባቢ ያለችሁ የኦሮሞ ህዝቦችና የኦሮሞ ተማሪዎች ከሌሎች ብሔር ብሔረሰብ የተውጣጡ ተማሪዎችን አቅፋችሁ፣ ፍቅር ሰጥታችሁ፣ ባህላችሁንና ቋንቋችሁን አስተምራችሁ ነገ እነዚህ ተማሪዎች የእናንተ አምባሳደር እንዲሆኑ ማድረግ ተገቢ ነው” ብለዋል ዶ/ር አብይ፡፡

በአንድነት ጠንክሮ በመስራት አገራችንን ብቻ ሳይሆን አፍሪካንም መቀየር እየተባባሩት እንደሚቻል የገለጹት ዶ/ር አብይ፣ አሁን ያለንበት ሁኔታን ጠንክሮ በመያዝ ኦሮሚያም ሆነ ኢትዮጵያ ያለ ምንም ጥርጥር መቀየር ይቻላል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “እስከ አሁን ችግር ውስጥ እንዲንቆይ ያደረገንም ሌብነት ስለሆነ ሌብነትን አጥፍተን በሀቀኝነት መስራት ከቻልን የዚህ አገር ሀብት እንኳንስ ለእኛ ለሌላውም የሚበቃ ነው” ብለዋል፡፡

“ሀብትን ለማፍራት መቁሰልና መሞት አስፈላጊ አይደለም፣ ያ ፋሽኑ አልፏል፣ ከዚህ በኋላ የሚያስፈልገው በሀሳብ ማሸነፍ ነው፣ ትናንት የሚፈለግብንን መስዋዕትነት ከፍለናል፣ የአሁን የሚያስፈልገው በፍቅር ማሸነፍ፣ ማቀፍ፣ መምከር፣ በሀሳብ አሸናፊ በመሆን ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ነው ” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ ለዩኒቨርቲው ያደረጉትን ክትትልና አመራርንም ዶ/ር አብይ አመስግነዋል፡፡

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram