በወልቂጤ በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን የጉራጌ ዞን አስተዳዳር አስታወቀ

በወልቂጤ ከተማ በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የጉራጌ ዞን አስተዳዳር አስታወቀ።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፈቱ ሰማን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ በተፈጠረው ግጭት የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።

ከዚህ በተጨማሪም በግጭቱ በሰባት ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱንም ተናግረዋል።

በግጭቱ ሳቢያም በርካታ የመኖሪያ ቤቶች እና ሱቆች መቃጠላቸውን እና ንብረት መውደሙንም ነው የተናገሩት።

በአሁኑ ወቅት የጸጥታ ሀይሎች ባደረጉት ጥረትም በአካባቢው መረጋጋት መፈጠሩንም ዋና አስተዳዳሪው አመልክተዋል።

የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች እና ህብረተሰቡም ችግሩን ለመፍታት እና ሰላም ለማስፈን ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

ኤፍ ቢ ሲ

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram