fbpx

በክረምት ወቅት አመጋገብዎ ምን መምሰል አለበት?

የክረምቱ ወቅት እየገባ እንደመሆኑ ያለውን ቅዝቃዜ ለመቋቋም እና ጤንነታችንን ለመጠበቅ ከሚረዱን ውስጥ አመጋገባችን አንዱ ነው።

ታዲያ በዚህ ወቅት ከአለባበስ ጀምሮ የምንከተለው አመጋገብ ወቅቱን በጤና ለመውጣት ወሳኝነት እንዳለውም ነው በተለያዩ ጊዜያትኑ ጥናቶች ያመለከቱት።

ሊከተሉት የሚገባ አመጋገብ፦

ሾርባ፦ ትኩስ ሾርባ በዚህ ወቅት ከምግብ ዝርዝርዎ ውስጥ ቢኖር ይመከራል፤ በተለያዩ የአትክልትና ስራ ስር ዘሮችም ይህን ማዘጋጀት ይቻላል።

ሰውነት የሚያስፈልገውን ከፍተኛ ሙቀት ለማግኘት ስለሚረዳ በዚህ ወቅት ተመራጭ አመጋገብ ነው።

በቆሎ፦ ወቅቱ እንደመሆኑ መጠን በቆሎ በየቦታው የማግኘት አማራጭ ይኖርዎታል።

ይህን አትክልት መንገድ ዳር ገዝቶ ከመመገብ ይልቅ ቤት ውስጥ ጠብሶ መመገብ።

ሙዝና እርጎ፥ የተላጠ ሙዝ በማዘጋጀት በጎድጓዳ ሳህን ውስጥ ከእርጎ፣ ቲማቲምና እንደ እንጆሪ ካሉ ፍራፍሬዎች ጋር በመቀላቀል መመገብ።

ከዚህ ባለፈም ሙዙን በጭማቂ መልክ በማዘጋጀትና ከተፈጨ ሩዝ ጋር በመቀላቀል በፈላ ውሃ አዘጋጅቶ የተወሰነ ማጣፈጫ በመጨመር መጠቀምም ይቻላል።

እንደ ድንች እና ቲማቲም ያሉ አትክልትና ስራ ስሮችን እንዲሁም ጥራጥሬዎችን በቆሎ መልክ በማዘጋጀት መመገብም ለዚህ ወቅት ተመራጭ ገበታ ነው።

ምግብ ላይ ጨው አለማብዛት፣ ውሃ ያላቸውን ምግቦች ማዘውተር፣ አትክልትና ፍራፍሬ ምርጫዎ ከሆነም ወቅታዊ የሆኑትን ብቻ ይመገቡ።
ከዚህ ባለፈም ትኩስ ነገር አዘጋጅተው ሲጠጡ በተቻለ መጠን ነጭ ሽንኩርት ቢጠቀሙ ይመከራል።

እነዚህን ማድረግዎ ለሰውነትዎ ሃይልና ብርታት እንዲያገኝ ይረዳዋል፥ ከዚህ ባለፈም በዚህ ወቅት የሚያስፈልገውን ሙቀትና የተለያዩ ማዕድናትና ቫይታሚኖችን እንዲያገኝ ያግዘዋል።

መመገብ የሌለብዎት፤

አትክልቶችን መመገብ መልካም ቢሆንም በተቻለ መጠን ወቅቱ ለተለያዩ ባክቴሪያና ጀርሞች መራቢያነት ምቹ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ይህን ማድረጉ
ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።

ስለዚህም እንደ ጎመን፣ ቆስጣ፣ ሰላጣና ጥቅል ጎመን ያሉ አትክልቶችን ቢቻል በዚህ ወቅት አለማዘውተር ካልሆነ ግን በደንብ አጥቦና አጽድቶ በማብሰል መጠቀም።

በጥሬው የሚዘጋጁ ፈሳሽ ጭማቂዎች፦ በዚህ ወቅት አየሩ የመታመቅ እድል ስለሚኖረው የሚዘጋጁ ፈሳሽ ጭማቂዎች ለተለያዩ በሽታ አምጭ ባክቴሪያዎች የመጋለጥ እድል አላቸው።

እናም ከተቻለ ወቅታዊ የሆኑ ፍራፍሬዎችን በመግዛት በደንብ አጥቦ ቤት ውስጥ አዘጋጅቶና በማቀዝቀዣ በማቆየት መጠቀም።

ተጠብሰውና ተዘጋጅተው የሚሸጡ ምግቦች፦ መንገድ ዳር ተዘጋጅተው የሚሸጡ እንደ ችፕስ፣ የአሳ ተዋጽኦዎች እንዲሁም ሌሎች ተዘጋጀተው የሚሸጡ ምግቦችን ማስወገድ ይገባል።

አሳ መመገብ ከፈለጉም በወጥ መልክ አዘጋጅተው ቢሆን ይመረጣል።

እነዚህን ምግቦች ሲመገቡ የሆድ መነፋትና ምቾት ማጣት እንዲሁም ማጣፈጫ ጨው ላያቸው ላይ የሚነሰነስ በመሆኑ በሰውነት ውስጥ ያለን ፈሳሽ በመቀነስ ለድርቀት ይዳርጋሉ።

ከሁሉም ግን መንገድ ዳር ተዘጋጅተው ከሚሸጡ ምግቦች ይራቁ።

ለስላሳ መጠጦች፦ እነዚህ መጠጦች በሰውነት ውስጥ ያለን ማዕድን የመቀነስ አቅም አላቸው፤ ይህ ደግሞ ሰውነት ያለውን ኢንዛየም እንዲያጣ ያደርገዋል።

የሚያቃጥሉ ምግቦች፦ በዚህ ወቅት ለአለርጅ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች እነዚህን ምግቦች መመገባቸው ከወቅቱ ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችልን አለርጅ ስለሚያባብስ አለማብዛቱ ይመከራል።

የስርዓተ ምግብ መፈጨት መስተጓጎል ደግሞ የዚህ ውጤት ይሆናል፥ ከቻሉ በዚህ ወቅት አይጠቀሟቸው፤ መሰል ችግር ካጋጠምዎት ግን የዝንጅብል ሻይ ይጠጡ።

ለሰውነት በሚከብድ መልኩ ከባድ የሚባሉ ምግቦችን አለመመገብም በዚህ ወቅት ይመከራል።

ምክንያቱም ከወቅቱ ጋር ተያይዞ በሰውነት ውስጥ የምግብ መፈጨት ስርዓቱ ዝግ ያለ በመሆኑ ምቾት የማጣት ስሜት ይፈጠራል።

ከዚህ ባለፈ ግን በዝናብ አለመመታትና በዝናብ የተመታን ልብስ በፍጥነት መቀየር እና ሰውነትን ማድረቅ።

በተቻለ መጠን እርጥበት የሚስቡ አለባበሶችን አለመጠቀምና ምግቦችን ብዙ ጊዜ አለማቆየትም ይመከራል።

ምንጭ፦ food.ndtv.com

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram