fbpx

በኬንያ በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለማስለቀቅ የመለየትና የጉዞ ሰነድ ዝግጅት እየተካሄደ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኬንያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት በሁለቱ ሀገራት መካከል እስረኞችን ለመልቀቅ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያውያን እሰረኞችን ከእስር ለማስለቀቅ የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ ነው።

እስካሁን ባለው ሂደትም የኬንያ የኢምግሬሽን ባለስልጣን እና ናይሮቢ የሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ዝርዝር የመለየት እና የጉዞ ሰነድ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ተገልጿል።

የመለየት ስራው እንደተጠናቀቀ ኢትዮጵያውያኑ እሰረኞች ከእስር ተለቀው ወደ ሀገር ቤት እንደሚመለሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሱዳን እና በሳዑዲ አረቢያ ባደረጉት ጉብኝት በተመሳሳይ በየሀገራቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከእስር እንዲለቀቁ ከሀገራቱ ጋር መስማማታቸው ይታወሳል።

በዚህም መሰረት በተለያዩ ምክንያቶች በሱዳን ታስረው የነበሩ 1ሺህ 400 ኢትዮጵያን ከእስር የተፈቱ ሲሆን፥ ወደ ሀገር በመመለስ ላይ ይገኛሉ።

በተመሳሳይ በሳኡዲ አረቢያ የሚገኙ ከ1 ሺህ በላይ እሰረኞችም ባሳለፍነው ሳምንት ከእስር መለቀቃቸው ይታወሳል።

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ምህረት ያደረገላቸው እና ከተለያዩ እስር ቤቶች የተለቀቁ 1 ሺህ 85 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram