በኦሮሚያ ክልል ዛሬ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ
ኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ፣በምዕራብ ወለጋ፣በምስራቅ ወለጋና በሆሮ ጉድሩ ወለጋ የሚገኙ አንዳንድ ከተሞች ውስጥ በዛሬው ዕለት በፀጥታ ኃይሎች በተወሰደ እርምጃ የሰው ሕይወት መጥፋቱን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
ዋሽንግተን ዲሲ — ጉደር ውስጥ አባትና ልጅ በጥይት መመታታቸውንና የአባትየው ሕይወት ማለፉን የቅርብ ጎረቤት ነኝ ያሉ ነዋሪ ገልፀውልናል። በአምቦም የሰው ሕይወት ጠፍቷል ተብሏል። በጊምቢ ሦስት ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በተጨማሪም በነቀምት፣በነጆ በመንዲና በአቅራቢያ ባሉ ከተሞች ውስጥ ውጥረ መንገሱን ነዋሪዎች ገልፀዋል።
መረጃውን ከመንግስት በኩል ለማጣራት የዞን ኃላፊዎች፣ የክልሉን መንግሥትና የፌደራል መንግስቱን ምላሽ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት አድርገን ነበር ስልካቸው ስለማይነሳ አልተሳካልንም።
Share your thoughts on this post