fbpx

በኢንዶኔዢያ በጀልባ መስጠም ምክንያት 166 ሰዎች የገቡበት አልታወቀም

በኢንዶኔዢያ በጀልባ መስጠም ምክንያት 166 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም፡፡

በኢንዶኔዢያ በሰሜናዊ ሱማትራ ቱባ በተባለው ሐይቅ የሚጓዙበት ጀልባ በመስጠሙ ምክንያት 166 ሰዎች የገቡበት አልታወቀም፡፡

ጀልባዋ አደጋ በገጠማት ወቅት አስቸጋሪ የአየር ንብረትና ሁለት ሜትር የሚደርስ አውሎ ንፋስ እንደነበረ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ጀልባው በእንጨት የተሰራች ስለመሆኗም የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

ምስሎች እንዳሳዩት ከሆነ በአንድ ሌላ ጀልባ የነፍስ አድን ጥረቶች ሲደረጉ እንደነበር የተነገረ ሲሆን፥ ዜጎች ግን ለተጎጂዎች ፈጣን ምላሽ አልሰጠም በሚል የሀገሪቱን መንግስት በመተቸት ላይ ይገኛሉ፡፡

ቶባ ሐይቅ በኢንዶኔዢ የሚገኝ ትልቅ ሐይቅ ሲሆን፥ በተለይ በኢድ አልፈጥር ወቅት በጎብኚዎች የሚዘወተር ቦታ ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ፦አልጀዚራ
በአብርሃም ፈቀደ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram