በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ14ኛው ሳምንትና አንድ ተስተካካይ ጨዋታ ትላንት ተካሂደዋል፡፡
ተስተካካይ ጨዋታቸውን ያደረጉት አዲስ አበባ ከተማ እና ሱሉልታ ሲሆኑ፥ አዲስ አበባ ከተማ ሱሉልታን 3ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በዚህም አዲስአበባ ከተማ በ26 ነጥብ ወደ ሁለተኛ ደረጃ መምጣት ችሏል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች ጨዋታቸውን ያካሄዱት ሱሉሉታ ከተማ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተላለፈበት ቅጣት ምክንያት አዳማ ላይ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
በሌሎች ጨዋታዎች ደሴ ከተማ አክሱም ከተማን 1ለ0፤ ፌደራል ፖሊስ ለገጣፎን 1ለ0 በሆነ ተመሳሳይ ውጤት አሸንፈዋል፡፡
ሊጉን ባህርዳር ከተማ በ13 ጨዋታዎች በ28 ነጥብ ሲመራ አዲስ አበባና ቡራዩ ከተማ በ26 እና በ24 ነጥቦች ተከታዩን ደረጃ መያዛቸው ተገልጿል፡፡
ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ
Share your thoughts on this post