fbpx

በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር አካባቢ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ግጭት ተፈጠረ

በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር አካባቢ ከዛሬ ጠዋት (ሰኔ 26) ጀምሮ ግጭት መፈጠሩ ተገለጸ።

የግጭቱ ምክንያት የሱዳን የጸጥታ ኃይሎች የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች የሚጠቀሙበትን የእርሻ መሬት እንዳያርሱ በመከልከላቸዉ በኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እና በሱዳን የጸጥታ ኃይሎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ነው ተብሏል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘላለም ልጃለም እንደተናገሩት፤ የእርሻ መሬቱን ለረጅም ዓመታት እየተጠቀሙበት የሚገኙት የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ናቸዉ፡፡ አሁን ግን የሱዳን አመራሮች ‹‹የእርሻ መሬቱን መጠቀም ያለብን እኛ ነን›› የሚል ሀሳብ አቅርበዋል፡፡ ሃሳቡ ተገቢነት የሌለዉ መሆኑንም ለአካባቢዉ የሱዳን አመራሮች አስረድተዋ፡፡ የሱዳን አመራሮች ግን ሃሳቡን ባለመቀበላቸዉ መግባባት አልተቻለም።

ግጭቱ የተከሰተዉ በመተማ ወረዳ ደለሎ ቁጥር 4 የእርሻ እና የኢንቨስትመንት ቦታ እና በሱዳን ባሶንዳ ዞን መካከል በሚገኝ ቦታ ነዉ፡፡

በግጭቱም ከሁለቱም በኩል ህይዎታቸዉን ያጡ እና የቆሰሉ መኖራቸዉ ተገልጿል።

ግጭቱን ለማረጋጋት የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ አካባቢዉ ተሰማርቶ በአሁኑ ወቅት አንጻራዊ መረጋጋት መፈጠሩንም አቶ ዘላለም ለአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት ተናግረዋል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram