fbpx

በኢራቅ ምርጫ ሙቅታዳ አል ሳዳር አሸነፉ

በኢራቅ ምርጫ የሺኣ እስልምናው የሰሪዮን ጥምረት መሪ ሞቅታዳ አል ሳድር በአብላጫ ድምፅ አሸነፉ፡፡

የምርጫ ኮሚሽኑ ይፋ ባደረገው መሰረት የስሪዮን ጥምረት 54 መቀመጫዎችን አሸንፏል፡፡

የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይድር አልአባዲ 42 ወንበሮችን በማግኘት ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

አልሳዳር ከኢራን ጋር ያላቸው ወዳጅነት እምብዛም ሲሆን፥ 47 ወንበር በማግኘት ሁለተኛ የወጣው ፋታህ ፓርቲ በአንጻሩ የኢራን ቀንደኛ ደጋፊ ነው ተብሎለታል፡፡

ከዚህ ቀደም አልሳዳር በ 2003 ኢራቅ ላይ ወረራ አካሂዶ የነበረውን የአሜሪካንን ጦር የሚፋለሙ ታጣቂ ነበሩ፡፡

አልሳዳር በዚህኛው የምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ሙስናን መታገል ዋነኛ ተግባራቸው አድርገው ስለመነሳታቸው ተነግሮላቸዋል፡፡

አሁን የተካሄደው ምርጫ በ2014 አብዛኛውን የኢራቅ ግዛት ተቆጣጥሮ የነበረውን አይኤስ አይኤስ ድል ካደረጉ በኃላ ሲካሄድ የመጀመሪያው ነው፡፡

ማሸነፋቸውን ተከትሎ የሺኣ እምነት እና የሰራዮን ጥምረት መሪው ሙቅታዳ አልሳዳር ሀገራቸውን ከገባችበት አጣብቂኝ አውጥተው ወደ ቀደመ ዝናዋ እንደሚመልሷት ታምኖባቸዋል።

ምንጭ፦ቢቢሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram