fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

በአፋር ክልል በተከሰተ የአተት በሽታ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ

በአፋር ክልል በተከሰተ የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አተት) በሽታ የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአፋር ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ።

ጤና ቢሮው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቀ የአተት በሽታው በክልሉ አራት ወረዳዎች ተከስቷል።

በክልሉ ጤና ቢሮ የህክምና ጤና ክብካቤ ዋና የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ሁሴን መሐመድ ሟቾቹ ከሚሌ ወረዳ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በአዋሽ ወንዝ ዳርቻ በሚገኙ ወረዳዎች የአተት በሽታ መስተዋሉ ተፋሰሱ በሚያቋርጣቸው 14 ወረዳዎች የመከሰት ዕድል ሊኖረው ስለሚችል ህብረተሰቡ ለአተት በሽታ ከሚያጋልጡ ድርጊቶች ራሱን እንዲከላከል ጠይቀዋል።

በሽታው የታየባቸውን ሰዎች የክልሉ ጤና ቢሮ ድንኳኖችን በመትከል ህክምና እንዲያገኙ እያደረገ ይገኛል።

የበሽታው ምልክት የታየባቸው ሰዎች በአቅራቢቸው ወደሚገኝ የጤና ተቋማት በማምራት የበሽታውን ስርጭት በመግታት እና በራስ ላይ የሚደርስ ጉዳት መከላከል እንደሚገባ አቶ ሁሴን አሳስበዋል።

 

 

በአሊ ሹምባህሪ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram