fbpx

በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መላክ የሌለብዎት ጉዳዮች

አንዳንድ ጊዜ ሰውን ለማስደመም ወይም ለቀልድ በሚል እሳቤ የተለያዩ የፅሁፍ መልፅክቶችን ሊላላኩ ይችላሉ።

እነዚህ የፅሁፍ መልዕክቶች ሳይታሰብ የግጭትና የጭቅጭቅ መንስኤ የሚሆኑባቸው አጋጣሚዎች ግን ብዙ ናቸው።

የስነ ልቦና ባለሙያዎችም ከጓደኛዎ አልያም ከፍቅር አጋርዎ ጋር የፅሁፍ መልዕክት በሚለዋወጡ ጊዜ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ይገልጻሉ።

ከዚህ አንጻርም እነዚህን ጉዳዮች በፅሁፍ መልዕክት ባይልኳቸው ይመረጣል ይላሉ ባለሙያዎቹ።

ቅሬታ፦ ምናልባት ወዳጅዎ ባልጠበቁት ሰዓት የፅሁፍ መልዕክት እንዳይልክልዎ ነግረውት ቢያደርገው እንኳን “የፅሁፍ መልዕክት እንዳትልክልኝ ብየህ ነበር” የሚል ምላሽ መልዕክት መላክ አይገባም።

ይህን በማድረጉም ቅሬታዎን መግለጽና ምናልባትም እያሾፍክ/እያሾፍሽ ነው የሚልና ተያያዥ ይዘት ያላቸውን መልዕክቶች አለመላክ፤ ከዚያ ይልቅ በአካል ተገናኝቶ መወያየት።

የስድብና ማመናጨቅ ይዘት ያላቸው መልዕክቶች፦ በሆነው ነገር ደስተኛ አለመሆንዎን በመግለጽ ማመናጨቅና የስድብ ይዘት ያላቸው የፅሁፍ መልዕክቶችን አለመላኩም ይመረጣል።

መልዕክትዎ በተቻለ መጠን ቀላልና ሲነበቡ ስሜት የሚነኩ መሆን አይገባቸውም።

ረጃጅም ማብራሪያዎችና ማብራሪያ አዘል የይቅርታ መልዕክቶች፦ አንድ ነገር ላለመከወንዎ ወይም ላለማድረግዎ በጣም እንደደከመዎትና በዚህ በዚህ ምክንያት ይህን ማድረግ አልቻልኩም በሚል ነገሮችን ለማስረዳት አይሞክሩ።

ከዚያ ይልቅ አጠር ባለ መልኩ በቀላሉ ይቅርታ አልያም ደግሞ መገናኘት እንችላለን ወይ? በማለት አጭር መልዕክት መላክን ምርጫዎ ያድርጉ።

ነገሮች ለምን እንዳልተደረጉ መጠየቅ፦ በዚህ መልኩ የሰዎችን ባህሪ ለማወቅ መሞከሩም ስህተት ነው።

እርስዎ ለላኩት መልዕክት ምላሽ አልተሰጠኝም በሚል ለምን አልመለስክልኝም/አልመለሽልኝም አልያም ደግሞ በእርስዎ እንደተበሳጩ ለማወቅ መጠየቁም በአጭር የፅሁፍ መልክት ብዙ አይመከርም።

ከበድ ያሉ ዜናዎች፦ ምናልባት ሰዎች ሳያስቡት ለማሳወቅ በሚል ከበድ ያሉ ዜናዎችን በጽሁፍ መላክ ማስወገድ ይኖርብዎታል።

ሌላው ቀርቶ በሰዎች ዘንድ መልካም ስሜት የሚፈጥረውን የመፈቀር ወይም የመፈለግን ጉዳይ አፈቅርሻለሁ/አፈቅርሃለው መልዕክትም ከፅጽሁፍ ይልቅ በአካል ቢሆን ይመረጣል።

ከባድ ርዕሰ ጉዳዮች፦ ምናልባትም የቤተሰብ ጉዳይ፣ የህጻናት ክብካቤ፣ የሂሳብና ተያያዥ ጉዳዮች፣ የጤና ጉዳዮች እና መሰል ከበድ ያሉ ርዕሰ ጉዳዮችን በጽሁፍ መልክዕት መለዋወጥ ለግንኙነትም ሆነ ለደህንነት ጠንቅ ነውና ያስወግዱት።

መሰል ጉዳዮችን በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ከማድረግ ይልቅ በአካል ተገናኝቶ በሰከነ መንፈስ መወያየትን ያስቀድሙ።

የግል ጉዳዮችን፦ ምናልባትም እርስዎ ጋር ብቻ ሊኖሩ የሚገባቸውን መረጃዎች በጣም አስቸኳይና አንገብጋቢ ቢሆን እንኳን ለሰዎች በፅሁፍ መልዕክት አሳልፎ መስጠት አይመከርም።

ለምሳሌ የቪዛ ካርድ የሚስጥር ቁጥር፣ ቤት ውስጥ ሲሆኑ የተነሷቸውና እርስዎ ጋር ብቻ መቅረት ያለባቸው ፎቶግራፍ ምስሎች እንዲሁም እንደ ኢሜልና መሰል አድራሻዎችን በፅሁፍ መልዕክትም ሆነ በኢንተርኔት አለመላላክ መልካም ነው።

ይህን ሲያደርጉ መረጃ በርባሪዎች ያለ እርስዎ እውቅናና ፈቃድ የእርስዎን መረጃዎች ሊያገኙና ችግር ሊፈጥሩ ስለሚችሉ መጠንቀቁን አይርሱ።

ሚስጥሮች፦ የእርስዎንም ሆነ የሌሎችን ሰዎች ድብቅ ሚስጥሮች በጽሁፍ መልዕክት መላላኩ ዋጋ ያስከፍላል።

ምናልባት የሚያውቋቸው ሰዎች ከሌሎች ጓደኞችዎ ተነጥለው በድብቅ የፍቅር ግንኙነት መጀመራቸውን በተመለከተ ለአንደኛው ወዳጅዎ ማካፈሉ ሌላ ጣጣ ሊያስከትል ይችላልና አያድርጉት።

እነዚያ ሰዎች ይህን ማድረጋቸው መልካም አይደለም ብለው ካሰቡ ጉዳዩን ፊት ለፉት ጠርተው መንገር እንጅ ለሌላ ሰው አሳልፎ መናገሩ እንደ ሃሜትም ስለሚታይ ያን አለማድረጉ ተመራጭ ነው።

ከላይ የተጠቀሱትን ጉዳዮች በማንኛውም አይነት የግንኙነት ደረጃ ላይ ከሆኑት ሰው ጋር በጽሁፍ መልዕክት መላላኩ የማይመከርና አላስፈላጊም ነው።

እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ በፅሁፍ መልዕክት ከመላላክ በአካል ተገናኝቶ መወያየት ብቸኛው አማራጭ መሆኑንም ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

መሰል ጥንቃቄዎች በፍቅር ህይዎትዎም ሊከተሏቸው የሚገቡ ናቸው።

ምንጭ፦ psychologytoday.com

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram