fbpx
AMHARIC

በአድዋ ድል ቀን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ

የአድዋ ድል በዓል በሚከበርበት ቀን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጸድቋል። የነቀምቴ እና ደምቢዶሎ ተቃውሞ፣ እንዲሁም ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ በሕክምና ስህተት ከህጻንነቱ አንስቶ ለ12 ዓመታት ራሱን ስለሳተው ኢትዮጵያዊ የተጀመረው የትዊተር ዘመቻን የሚመለከቱ አስተያየቶችን አሰባስበናል።

በዓለም ዙሪያ ዝናን ያተረፈው «ብላክ ፓንተር» የተሰኘው የሆሊውድ ፊልም ዛሬ ከተከበረው የአድዋ ድል ጋር ምን ያገናኘዋል? ስለዚሁ ጉዳይ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የተጻፉ ነጥቦችን ዳሰናል። የድል በዓሉን እያወደስን እያሰማን ከፊልሙም እያጣቀስን እንዘልቃለን። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተነገረ በኋላ በነቀምቴ እና በደምቢዶሎ ስለነበረው ተቃውሞ እና የጸጥታ ኃይላት ርምጃም አስተያየቶችን አሰባስበናል። የምክር ቤት አባላት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዳያጸድቊ ስለነበረው ውትወታም የተጻፉትን እናካትታለን።

ዋሽንዘዴዎች የተጻፉየአፍሪቃ እውነተኛ ዋካንዳ እና ቅኝ ላለመገዛት ተጋድሎው» ሲል ማክሰኞ ዕለት ለንባብ ያበቃው ጽሑፉ የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት ምንጭ የኾነውን የአድዋ ድል ይዘክራል።  «ዋካንዳ» ሰሞኑን በዓለም ዙሪያ የበርካቶች መነጋገሪያ የኾነው «ብላክ ፓንተር» የተሰኘው የሆሊውድ ፊልም ታሪክ የሚፈጸምባት ከተማ ናት።

ይህች አፍሪቃ ውስጥ የምትገኝ ምናባዊ ከተማ በሥልጣኔ ጫፍ የደረሰች፤ በጥበቧ ራሷን ከዓለም ሰውራ የምትኖር፤ ፈጽማ በቅኝ ያልተገዛች ናት ፊልሙ ውስጥ በሚነገረው ታሪክ።  ከዋካንዳ በተለየ መልኩ ግን ኢትዮጵያ ነጻነቷን ጠብቃ የቆየችው በአስማታዊ ንጥረ-ነገር ሳይኾን በጀግኖች ተጋድሎ ነው ይላል ጽሑፉ። ዋሽንግተን ፖስት ሲቀጥል፦ በእርግጥም አውሮጳውያን ቅኝ ገዢዎች በ19ኛው ክፍለ ዘመን አፍሪቃን ሲቀራመቱ ኢትዮጵያ በነጻነቷ ጸንታ የዘለቀች ልዩ ሀገር ናት ይላታል። ኢትዮጵያ በቀድሞ አጠራሯ አቢሲኒያ በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ለአውሮጳውያን ምሥጢር የነበረች መኾኗ ከዋካንዳ ጋር በመጠኑ ያመሳስላታል ሲልም አክሏል።

በርካቶች በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች በተቀባበሉት በዚህ የዋሽንግተን ፖስት ዘገባ ላይ  የተጠቀሰው ደብርሀን የተባለው ድረ-ገጽ  ስለ ዋካንዳ እና የኢትዮጵያ ነጻነት በዝርዝር ጽፏል። በ«ብላክ ፓንተር» ፊልም ላይ አብይ ገጸ ባሕሪው ንጉሥ ቲ ቻላ ከንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምንሊክ ጋር እንደሚመሳሰል ደ ብርሀን ገልጧል። ቲ ቻላን ከኢትዮጵያ ንጉሥ ጋር የሚያመሳስለው በርካታ ነገሮች አሉ ያለው ደብርሀን፤ ቲ ቻላ በልጅነቱ ተጠልፎ መወሰዱ እና አውሮጳውያን ወራሪዎችን ድል ነስቶ ሀገሩን  ከቅኝ ግዛት  መታደጉን ይጠቅሳል። ዳግማዊ ዓጼ ምንሊክም የ11 ዓመት ልጅ ሳሉ በንጉሠ-ነገሥት ቴዎድሮስ ተጠልፈው መወሰዳቸው በአድዋ ድልም ለአፍሪቃውያን ኩራት መኾናቸውን በማነጻጸር ያቀርባል። ደ ብርሀን ከጽሑፉ ጋር አያይዞ ያቀረባቸው የሌሎች ሰዎች የትዊተር መልእክቶችም ተመሳስሎውን የሚያጠናክሩ ናቸው።

ኤም ኤንድ ጂ ፍራይዴይ የተባለው የትዊተር ገጽ፦ «የዋካንዳ ታሪክ ሊነጻጸር የሚችለው ከኢትዮጵያ ጋር ብቻ ነው» ብሏል። ፕሮፌሰር ካንትቦት በሚል የትዊተር መጠሪያ፦ «ብላክ ፓንተር» እና «ዋካንዳ» እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ1759 በሣሙኤል ጆንሰን ከተጻፈው ራሴላስ ከተሰኘው ልብወለድ የተዘረፈ ታሪክ እንደኾነ ገልጧል። የራሴላስ ታሪክም የሚያጠነጥነው  በሥነ-ቴክኒክ በመጠቀው ድብቅ ንጉሣዊ ግዛት ይኖር የነበረው ኢትዮጵያዊ ልዑል በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ወንበዴዎችን እና ቀማኞችን ሲፋለም እንደኾነ ጠቅሷል። «አዝናለሁ፤ ንጉሦች የራሳችሁን ሐሳብ አመንጩ» ሲል አክሏል።

የአዲስ ስታንዳርድ ድረ-ገጽ ዋና አርታኢ ፀዳለ ለማ በትዊተር ገጿ፦ የፊልሙ ደራሲ ስታን ሊ ከቅኝ ግዛት ነጻ የኾነችው «ዋካንዳ»ን ሲፈጥር በአዕምሮው የነበረችው ኢትዮጵያ «ትመስለኛለች» ብላለች። የፀዳለም የትዊተር መልእክት በዋሽንግተን ፖስት ጽሑፍ ተጠቅሷል።

ዮሐንስ ሞላ በፌስቡክ ገጹ፦ «መጣልኝ አድዋ ነፍስና ስጋዬን ሊለያያት… የድሉን ታሪክ ታይቶ እንደማያውቅ፣ ነፍስና ስጋ ዘርቶበት መላ አካልን ውርር የሚያደርገውን የጂጂዬን ሙዚቃ እየሰማው ልቆዝም፣ በእህህታ “ዛሬስ የት ነን? ምንስ እናደርጋለን?” ብዬ ልብከነከን» ሲል ብሏል።

“ሂድ!…ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያርግልህ! እግሩን ለጠጠር፣ ደረቱን ለጦር አስጥቶ ደሙን ለሀገሩ ፍቅር አፍስሶ፣ ለአፈሩ ክብር አፈር ለብሶ እሱ ወድቆ ሀገሩን የማያቆም እዚህ ያለ እንዳይመስልህ!” እቴጌ ጣይቱ ብጡል ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ» አማኑኤል ተስፋዬ በትዊተር ያሰፈረው ከታሪካዊ ተውኔት የተቀነጨበ ጽሑፍ ነው።

ሔዋን ዘ ስምዖን፦ አድዋ የአሜሪካ ድል ቢኾን ኖሮ በሺህ የሚቆጠሩ የተለያዩ አይነት ፊልሞች ይሠሩ እንደነበር ትዊትር ገጽ ላይ ጠቅሳለች።  «ቢያንስ አድዋ እራሱ መኖሩ ለኛ መጽናኛ ነው-ጉራም አንወድም ምናምን ብለን እንለፈው እንጂ» ብላለች።
«ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ፣ የጣልያን ባሪያ እንጅ ባልተባልኩ ሐበሻ፣ አደዋ አድዋ አድዋ» ያለው ደግሞ ባይለኝ ቦጋለ ነው።

«‏እንኳን ለአድዋ ድል 122ኛው ዓመት ክብረ በዓል አደረሰን» ያለው ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 በትዊተር ገጹ፦  «ስለአድዋ ምን ያውቃሉ?» ሲል ጠይቋል። «ታላቁ የአድዋ ድል በዓል የሚከበርበት የአፄ ምኒሊክ ሐውልት የቆመው ከአድዋ ጦርነት 35 ዓመታት በኋላ ጥቅምት 22፣ 1923 ዓ.ም መሆኑን ያውቃሉ?» ሲልም አክሏል።

«አድዋ የአፍሪቃዊያን ኩራት» ያብ ሲሳይ ማማሩ የፌስቡክ አጭር መልእክት ነው። ቀጣዩ አጫጭር መልእክቶችም በፌስቡክ የተሰጡ ናቸው። «አድዋ የኛነታችን መኩሪያ!»  ያለው አህመድ ሐምዛ ሲኾን፤ ቶፊቅ ሀሰን «…አድዋ የኛነታችን መለያ» ብሏል። «አድዋ የኢትዮጵያውያን አንድነት» በሐብታሙ ባርጎባ የተሰጠ አስተያየት ነው። ፀጋው መላኩ፦ «ኢትዮጵያዊነት ወደ መሥመሩ እየተመለሰ ነው፤ አድዋ» ሲል በእንግሊዝኛ ጽፏል እዛው ፌስቡክ ላይ።

ነቀምቴ እና ደምቢዶሎ ውስጥ ከባለፈው ሳምንት ማብቂያ ጀምሮ በነበረው ተቃውሞ ድምፃቸዉን ለማሰማት መንገድ ላይ በወጡ ሰዎች ላይ የመከላክያ ሰራዊት አባላቶች ተኩስ እንደከፈቱባቸዉ የከተማዋ ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችም ስለተቃውሞው ተጽፏል።

እኔስ ለሀገሬ የተሰኘው የፌስቡክ ገጽ፦ «የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት በማድረግ ህዝብን ለመግደል የተሰማራውን የህውሐት አግዓዚ ጦር የሚፈጽመው ግድያ ይቁም» ሲል ጽፏል። «ከተማ ለቆ ድንበር ይጠብቅ፣አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አንቀበልም የሚሉ ተቃውሞዎች በነቀምትና ደንቢዶሎ ተደረገ« ሲልም ተቃውሞውን የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን አያይዟል።
የምክር ቤቱ አባላት በተለይም የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች አዋጁን ውድቅ እንዲያደርጉ ከአገር ዉስጥም ሆነ ከዉጭ ጫና እየተደረገባቸዉ መኾኑም በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች ሲዘገብ ነበር። የአስቸካይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ባወጣዉ መግለጫ ይህን ጉዳይ «በቸልታ እንደማይመለከተው» እና በጫና በሚድረጉ ቅስቀሳ የሚሳተፉ ላይ «ሕጋዊ ርምጃ» እንደሚወስድ አስጠንቅቋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በአብላቻ ድምፅ አጽድቋል።

ሻናን ካዎ «ወያኔዎች ማስፈራራት ልማዳቸው ነው እነደነሱ ፋሪ ካገኙ አሁን በሚድያ ይፋ ስላደረጉ ነው እንጅ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ የኦሮሞ ህዝብ ኮማንድ ፓስት ከታወጀበት 27 ዓመቱ ነው» ሲል ጽፏል። ፍትዊ ዘ መሀሪ ደግሞ እዛው ፌስቡክ ላይ ፦«እና ወሮበላ አገሪትዋን ይበጥብጣት» በማለት ጠይቋል።

«ፍትኅ ለብላቴናው መሀመድ» በሚል የተደረገው የትዊተር ዘመቻ ሌላኛው የማኅበራዊ መገና ዘዴዎች ርእስ ነው።
ሃይከል ትዊተር ላይ ባሰፈረው የእንግሊዝኛ መልእክቱ «በሕክምና ስህተት ተብዬ ኢትዮጵያዊው ህጻን ራሱን ስቷል። የሚኖረውም ጂዳ ነው» ብሏል። «ይኽ እጅግ አስደንጋጭ ነው፤ ልብም የሚሰብር» ሲል  አክሏል። በሐኪም ቤት የመኝታ ክፍል ውስጥ ጥቊር ሻሽ ጠምጥመው ጥቊር መቅለሚያ የደረቡት ኢትዮጵያዊት እናት አልጋው ላይ ራሱን ስቶ በጸጥታ የተኛውን ልጃቸውን ጭንቅላት ይዘው ሲስሙት ይታይል። የእናቲቱ ገጽ በሐዘን ተኮማትሯል።

ኢትዮጵያያዊቷ እናት ወ/ሮ ሐሊማ ሙዛሚል ሁሴን የዛሬ 12 ዓመት ስለኾነው ለዶይቸ ቬለ እንደተናገሩት ልጃቸው ሐኪም ቤት ሲገባ ጤነኛ ነበር። «ልጄ ሞሐመድ አብደልአዚዝ ያህያ እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2006 የአራት ዓመት ሕጻን ሳለ ወደ ሐኪም ቤቲ የሄደው በእግሩ እየተራመደ ነበር» ብለዋል።

እናት በስህተት ልጃቸው ለዓመታት አቅሉን ስቶ ለአልጋ በመዳረጉ የ2,4 ሚሊዮን የሳውዲ ሪያል ገንዘብ ካሣ እንዲሰጣቸው ተወስኖላቸው ነበር።  ይኹንና ሐኪም ቤቱ ገንዘቡን የሚሰጣቸው የህይወት ማቆያው ተነቅሎ ልጃቸውን ከወሰዱ መኾኑን ሲነግራቸው ሳይስማሙ ቀርተዋል።  ልጃቸው አኹንምmH,ኪም ቤት አልጋ ላይ ይገኛል።

ለዓመታት የሞሐመድን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተለው ጋዜጠኛ ነቢዩ ሲራክ «”ያገባኛል ” የሚል ተቆርቋሪ ዜጋ ያስፈልገናል! ድምጽ ለሌለው ፣ ለማያይ ለማይሰማና ለማይናገረው ብላቴናው መሐመድና ለከልታማ ቤተሰቦቹ መገፋት መብት ማስከበር መቆም ዋጋ አለው!  ፍትህ ለብላቴናው መሀመድ» ሲል ትዊተር ላይ ጽፏል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ – DW

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram