fbpx

በአዳማ ኩሪፍቱ ሪዞርት ላይ በኤሌክትሪክ ምክንያት የእሳት አደጋ ደረሰበት

በአዳማ ከተማ እሬቻ ቀበሌ በሚገኘው ኩሪፍቱ ሪዞርት ላይ የደረሰ የእሳት ቃጠሎ አዳጋ በንብረት ላይ ጉዳት ማስከተሉን የከተማው ፖሊስ መመሪያ አስታወቀ።

የከተማው ፖሊስ መመሪያ የህዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ ምክትል ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ እንደገለጹት፥ ትላንት ከረፋዱ 4 ከ30 ሰዓት አካባቢ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ በሪዞርቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

በተከሰተው የእሳት ቃጠሎ በሪዞርቱ ውስጥ የነበረው ንብረት ሙሉ በሙሉ መውደሙን ምክትል ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልጸዋል።

ከሁለት ሰዓት በላይ የፈጀውን የእሳት ቃጠሎ ለመቆጣጠር ሕብረተሰቡ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት፣ የፌዴራል ፖሊስና የኦሮሚያ የፖሊስ አባላት ከፍተኛ ርብርብ በማድረጋቸው እሳቱ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

በተጨማሪም አደጋውን ለመቆጣጠር ከሞጆ ደረቅ ወደብ፣ ከቢሾፍቱ አየር ኃይል፣ ከትራክተር ፋብሪካና የከተማው መስተዳድር የእሳትና አደጋ መከላከያ ሠራተኞች ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸውን ምክትል ኢኒስፔክተር ወርቅነሽ አስረድተዋል።

አደጋው በአካባቢው የነበረው ትራንስፎርመር ፈንድቶ የኤሌክትሪክ ኬብል በሳር ቤቶች ላይ በመውደቁ የተነሳ የተከሰተ መሆኑንም ገልጸዋል።

በቃጠሎው የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳይ ለማወቅ ኮማንድ ፖስት፣ ፖሊስና የሪዞርቱ ባለቤት በማጣራት ላይ መሆናቸውንም ተመልክቷል።

ምንጭ፡-ኤፍ.ቢ.ሲ
Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram