በአዲስ አበባ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የመንግስት ሠራተኞች ቤት ለመስጠት ምዝገባ ተጀመረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የመንግሥት ሠራተኞችን የመኖርያ ቤት ባለቤት ለማድረግ በየወረዳው ምዝገባ ጀመረ።

በወጣው መስፈርት መሠረት ወርሐዊ ገቢያቸው ከብር 2001 እስከ 3500 የሆኑ ቋሚ እና በአስተዳደሩ መ/ ቤቶች ከአምስት ዓመት በላይ ያገለገሉ የመንግሥትሠራተኞች የዕድሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ።

ከወርሀዊ ደመወዝ ብር 2001 በታች እና ከብር 3500 በላይ ያሉት የመንግሥት ሠራተኞች በዚህ ኘሮግራም ለምን እንዳልታቀፉ የታወቀ ነገር የለም።

አስተዳደሩ ለመስጠት ያሰበው ቤት ምን አይነት እንደሆነ የተሰጠ ዝርዝር መግለጫ እስካሁን አለመኖሩም ታውቋል።

News.et

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram