fbpx

በአውሮፓ የአሜሪካ የዜና ምንጮች በአህጉሪቷ ድረገጾች ላይ እንዳይታዩ ታገዱ

የአውሮፓ ህብረት የመረጃ ከለላ ህግን በስራ ላይ በማዋሉ ምክንያት ታዋቂነትን ያተረፉ የአሜሪካ የዜና ምንጮች በአህጉሪቷ ድረገጾች እንዳይታዩ ታገዱ፡፡

በአውሮፓ በሚገኙ ሀገራት ከታገዱት የዜና ምንጮች መካከል ቺካጎ ታይምስና ሎስአንጀለስ ታይምስ ይገኙበታል ተብሏል፡፡

አጠቃላይ የመረጃ ከለላ መመሪያ በሚል የወጣው ህግ ለአውሮፓውያን ዜጎች በመረጃ አጠቃቀም ዙሪያ ተጨማሪ መብት ያጎናጽፋል ተብሏል፡፡

አሁን የወጣው ህግ የአውሮፓ የህግ አውጪዎች የቴክኖሎጂ ካምፓኒዎችን አቅም ለመገደብ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ህጉ በ21 ስቴቶች 46 ዕለታዊ ጋዜጦችን በማሳተም የሚጣወቀውን ሊ ኢንተርፕራዝንና ሌሎቹንም የዜና ምንጮች ላይ ጉዳት ያደርሳል ተብሏል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ህጉ ወደ ስራ መግባቱን አስመልክቶ በለቀቀው የትዊተር መልእክት አውሮፓውያን መረጃዎቻቸውን እንዲቆጣጠሩ ያስችላል በተጨማሪም የአህጉሪቷን የዲጂታል ሉአላዊነት ያረጋግጣል ብሏል፡፡

 

ምንጭ፦ቢሲሲ
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram