fbpx

በአሪዞና የሚገኙ ተላላኪ ሮቦቶች ከእግረኞች እኩል መብት ተሰጣቸው

በዩናይትድ ስቴትስ አሪዞና ግዛት ውስጥ የሚገኙ የእግረኛ መንገድ ተጠቃሚ ተላላኪ ሮቦቶች ከተጓዦች እኩል መብት ተሰጣቸው፡፡

ከዚህ ቀደም ሞተር ሳይክልን ጨምሮ ሮቦቶች እንዲሁም ሌሎች የቴክኖሎጂ ውጤቶች እግረኛ መንገድ እንዳይጠቀሙ የሚል ህግ ነበር፡፡

በዚህ ወር መጀመሪያ ታዲያ በአሪዞና ገዢ የጸደቀው አዲስ ህግ የእግረኛ መንገድን እንዲጠቀሙ የሚፈቅድ ነው፡፡

አዲስ የወጣው ህግ በአሪዞና የሚገኘውን የተላላኪ ሮቦቶችን ገበያ የበለጠ ያሻሽለዋል ተብሏል፡፡

ደንበኞች በአፕሊኬሽን በመታገዝ ምግቦችን አበባዎችን ቡና እንዲሁም ሌሎች ትዕዛዞችን ባዘዙ በደቂቃዎች ውስጥ ያደርሳል ነው የተባለው፡፡

የድርጅቱ ቃልአቀባ የሆኑት ሄንሪይ ሃሪስ-በርላንድ ተላላኪ ሮቦቶቹ በአምስት ሀገራት በ10 የተለያዩ ከተማዎች ውስጥ አገልግሎት እንደሚሰጡ አስታውቀዋል፡፡

ሄንሪይ እንዳሉት ከሆነ ደንበኛው በአካባቢ በሚገኙ መደብሮች ውስጥ የሚፈልገውን ዕቃ ከአፕሊኬሽን ላይ ከመረጠ በኃላ ትዕዛዙን ያስተላልፋል፤ ከዚያም ሮቦቶቹ ከ15 እስከ 30 ደቂቃ ትዕዛዙን ያስረክባሉ ነው ያሉት፡፡

ይህንን ንግድ ጀመሩት ሁለት የስካይፒ ተባባሪ መስራቾች ሲሆኑ፥ በዘርፉ የሚታየውን ችግር ካስተዋሉ በኃላ ነው ተብሏል፡፡

ሆኖም አንዳንድ ደንበኞች በቴክኖሎጂው ቢደሰቱም ሌሎች ደግሞ የእግረኛውን መንገድ በቅርብ ዓመታት ውስጥ እንደማያጨናንቁት በምን እርግጠኛ ልንሆን እንችላለን ብለዋል፡፡

 

 

ምንጭ፦ ፎክስኒውስ
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram