fbpx

በአለም ዋንጫው ናይጄሪያ ከአርጀንቲና ይገናኛሉ

በሩሲያ እየተካሄደ በሚገኘው 21ኛው የአለም ዋንጫ በዛሬው ዕለቱ በተለያዩ ጨዋታዎች ቀጥሎ ይውላል።

በከፍተኛ ሁኔታ ተጠባቂ የሆነው በምድብ አራት ናይጀሪያን ከአርጀንቲና የሚያገናኘው ጨዋታ ምሽት 3 ሰዓት ላይ ይካሄዳል።

ናይጀሪያ በሁለት ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ በመያዝ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን፥ አርጀንቲና በተመሳሳይ ጨዋታና በሶስት የግብ እዳ አንድ ነጥብ በመያዝ በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

በሌላ ጨዋታ ምድቡን በቀዳሚነት የምትመራውና ማለፏን ያረጋገጠችው ክሮሺያ ከአይስላንድ በተመሳሳይ ምሽት 3 ሰዓት የምትገናኝ ይሆናል።

በምድቡ ናይጀሪያ ከአርጀንቲና አቻ የምትለያይ ከሆነና አይስላንድ በክሮሺያ የምትሸነፍ ከሆነ ንስሮቹ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን ማረጋገጥ ይችላሉ።

በሌላ በኩል አርጀንቲና ናይጀሪያን የምታሸንፍ ከሆነና አይስላንድ በክሮሺያ የምትሸነፍ ወይም አቻ የምትወጣ ከሆነ የአለም ኮኮቡን በቡድኗ ያካተተችው አርጀንቲና ማለፍ ትችላለች።

ይህንም ተከትሎ የአለም ኮከቡን በቡድኗ ያካተተችው አርጀቲና ከናይጀሪያ የሚያገናኘው ጨዋታ ተጠባቂ ሆኗል።

በዛሬው ዕለት በአለም ዋንጫው በምድብ ሶስት ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ሁለት ጨዋታዎች የሚካሄዱ ይሆናል።

በዚህም የምድቡ መሪ የሆነችው ፈረንሳይ ከዴንማርክ ስተገናኝ አውስትራሊያ ከ ፔሩ ትጫወታለች።

ከምድቡ ማለፏን ያረጋገጠችው ፈረንሳይ ከዴንማርክ የሚያደርጉት ጨዋታ የሚጠበቅ ሲሆን፥ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ዴንማርክ ከፈረንሳይ አንድ ነጥብ ማግኘት ከቻለች ወደ ቀጣዩ ዙር ማሏን ታረጋግጣለች።

እንዲሁም በምድቡ አንድ ነጥብ በመያዝ በሶስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው አውስትራሊያ ፔሩን ሶስት ግብ በማስቆጠር ካሸነፈች እና ዴንማርክ በፈረንሳይ ከሁለት ግብ በላይ ተቆጥሮባት የምትሸነፍ ከሆነ አውስትራሊያ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን ታረጋግጣለች።

በሩሲያ እየተካሄደ ባለው 21ኛው የአለም ዋንጫ በትናትናው ዕለት ኡራጋይ፣ ሩሲያ፣ ስፔን እና ፖርቹጋል ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram