በናይጄሪያ በተፈፀመ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት 31 ሰዎች ሞቱ

በናይጄሪያ ቦኖ ግዛት በተፈፀመ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት የ31 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃቱ የተፈፀመው የሀገሪቱ ጦር ዋና አዛዥ አካባቢው ሰላም መሆኑን በመጥቀስ ተፈናቅለው የነበሩ ሰዎች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ መጠየቃቸውን ተከትሎ በሰዓታት ልዩነት ውስጥ ነው።

በቦኖ ግዛት በምትገኘዋ ዳንቦታ ከተማ በተፈፀመው የእጥፍቶ ጠፊ ጥቃትም በትንሹ 31 ሰዎች ሲሞቱ፤ በርካታ ሰዎች ላይ ደግሞ የመቁሰል አደጋ ደርሷል።

ወደ ከተማዋ በተከታታይ ሮኬቶች ከከተኮሱ በኋላ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቱ እንደተፈፀመም ተገልጿል።

ለጥቃቱ እስካሁን ሀላፊነት የወደሰ ወገን ባይኖርም፤ ጥቃቱን የፈፀሙት የቦኮ ሀራም ታጣቂዎች እንደሆኑ ተጠርጥሯል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram