fbpx

በኒው ደልሂ በተቀሰቀሰ መርዛማ አቧራ ነዋሪዎች እየተቸገሩ ነው

በኒው ደልሂ በተቀሰቀሰው መርዛማ አቧራ ነዋሪዎች እየተቸገሩ መሆኑ ተገልጿል።

አሁን ላይ የህንዷ ከተማ ኒው ደልሂ በአቧራ የተሸፈነች ሲሆን፥ ነዋሪዎቹ ለመተንፈስ እየተቸገሩ መሆኑና በከተማዋ መኖር ለህይወታቸው አስጊ መሆኑ ነው የተገለጸው።

በዚህም የሀገሪቱ መንግስት የኮንስራትክሽን ስራዎች እንዲቆሙና የአሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች በከተማዋ እየተዘዋዎሩ ውሀ እንዲረጩ አድርጓል ተብሏል።

ነዋሪዎቹም ከቤተታቸው እንዳይወጡ ጥሪ መተላለፉም ታውቋል።

ኒው ደልሂ በአቧራ ከመኘፈኗም በላይ ከዚህ ቀደም ከነበርው የከተማዋ አየር ብክለት ከ8 – 9 እጥፍ ብልጫ ያለው የአየር ብክለት ተመዝግቧል ነው የተባለው።

በዚህም ሰዎቹ አየር በሚስቡበት ወቅት ይሄው መርዛማ ነገር ወደ ውስጣቸው በመግባት ለጤናቸው አደገኛ መሆኑን የከተማዋ የአካባቢ ሳይንስ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አኑሚታ ሮይ ቾውንሁሪ ገልጸዋል።

ደልሂ በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ነዋሪዎች ከሚኖሩባት ከተሞች አንዷ ስትሆን አሁን ላይ የከባቢ አየር ብክለት የነዋሪዎችን ምቾት እየነሳ መሆኑ ተመላክቷል።

ይህ አቧራ በከተመዋ አካባቢ ከሚገኘው ራጃስታን በረሃ ሊነሳ እንደሚችል የዘርፉ ባለሞያዎች አስተያየታቸውን መስጠታቸውን ዘገባው አመላክቷል።

የአየር ብክለቱም በሂደት እየተባባሰ መምጣቱን የተገለጸ ሲሆን፥ የዓለም ጤና ድርጅት ለሰዎች ልጆች ህይወት ተስማሚ ነው ብሎ ካስቀመጠው ስታንደርድ የ 30 ያህል እጥፍ ብልጫ እንዳለው ነው ዘገባው የሚያስረዳው።

 

 

ምንጭ፦ bbc.com

የተተረጎመው፦ በእንቻለው ታደሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram