fbpx

በተለያዩ ምክንያቶች በሱዳን ታስረው የነበሩ 1ሺህ 400 ኢትዮጵያን ተፈቱ

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለፋና ብሮስድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ እንደገለጸው ኢትዮጵያኑ የተፈቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሱዳን ጉብኝታቸው ወቅት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እነዚህ ኢትዮጵያን እንዲፈቱ ለሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሳን አልበሽር ጥያቄያቸውን አቅውርበው እንደነበረ የሚታወስ ሲሆን፥ የጠ/ ሚኒስትር ዶክተር አብይን ጥያቄ የተቀበሉት ፕሬዝዳንት አልበሽር ፕሬዝዳንታዊ አዋጅ አውጥተው በሱዳን የታሰሩ ኢትዮጵያን እንዲፈቱ ማድረጋቸው ነው የተገለጸው።

የተፈቱት ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የሱዳን እስር ቤቶች ይገኙ የነበሩ መሆናቸውም ተገልጿል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram