fbpx

በቦክስ አዲስ ታሪክ ያስመዘገበችው ከወጣቷ ቦክሰኛ ሀና ደረጄ ጋር ቆይታ

ለተከታታይ 6 ቀናት በሞሮኮ ትልቋ ከተማ ካዛብላንካ ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ወጣቶች ቦክስ ሻምፕዮና ኢትዮጵያዊቷ ሀና ደረጀ ድል ቀንቷታል። በ45 ኪ.ግ ኢትዮጵያን በመወከል የተወዳደረችው ሀና የአልጀርያ ተወዳዳሪን በፍፁም የበላይነት አሸንፋለች ።

በዚህም በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ኢትዮጵያን በመወከል በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ የዓለም ወጣቶች ኦሎምፒክ የምትሳተፍ የመጀመሪያዋ ሴት ቦክሰኛ መሆኗን አረጋግጣለች ። ከጅግጅጋ ከተማ የተገኘችው ሀና ደረጀ በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ የ4 ተኛ አመት ሰልጣኝ ናት:: ሀገር ውስጥ በሚደረጉ ውድድሮች ጠንካራ ፉክክር በማድረግ በርካታ ድሎችን መቀዳጀት ችላለች።

ሀና ደረጀ በዚህ አመት መጨረሻ ከወጣቶች አካዳሚ ስልጠናዋን አጠናቃ የምትመረቅ ሲሆን በቦሌ መሰናዶ ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪ ናት። በሞሮኮ ካዛብላንካ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ወጣቶች የቦክስ ውድድር ኢትዮጵያን የወከለቸው ሀና ደረጀ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘች።

ሀና ከ45 እስከ 48 ኪሎ ግራም ዛሬ ባካሄደችው የፍጻሜ ጨዋታ የቱንዚያ አቻዋን በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች። ውድድሩን በማሸነፏ በጥቅምት ወር 2010 ዓ.ም በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በሚካሄደው የዓለም ወጣቶች ኦሎምፒክ ተሳትፎዋን ማረረጋገጧን የኢትዮጵያ የቦክስ ፈዴሬሽን የውድድርና ስልጠና ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ስንታየሁ ተስፋዬ ለኢዜአ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ሀና ደረጀ በነሐሴ ወር 2010 ዓ.ም በሀንጋሪ ቡዳፔስት በሚካሄደው የዓለም ወጣቶች የቦክስ ውድድር እንደምትሳተፍ ጠቅሰዋል። የዓለም ወጣቶች ኦሎምፒክ መሳተፍ የሚችለው በአፍሪካ የቦክስ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ሲያገኝ ብቻ እንደሆነም አስረድተዋል።

በዚህ የአፍሪካ ወጣቶች የቦክስ ውድድር በሴቶች ኢትዮጵያን ወክላ በብቸኝነት የተካፈለችው ሀና ባለፈው ሳምንት ከ45 እስከ 48 ኪሎ ግራም  የአልጀሪያ ተጋጣሚዋን ማሸነፏን አስታውሰዋል። ሀና ደረጀ የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ ያፈራት ተወዳዳሪ ናት። በ49 ኪሎ ግራም ለፍጻሜ የተወዳደረው እንዳሻው አላዩ በአሁኑ ሰአት ከአልጄሪያ አቻው ጋር የፍጻሜ ጨዋታ እያደረገ ይገኛል።

በውድድሩ ላይ ኢትዮጵያን ወክለው ግማሽ ፍጻሜ የደረሱት እንዳሻው አላዩና ተመስገን ምትኩ በነሐሴ ወር 2010 ዓ.ም በሀንጋሪ ቡዳፔስት በሚካሄደው የዓለም ወጣቶች የቦክስ ውድድር መሳታፋቸውን አረጋግጠዋል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram