fbpx
AMHARIC

በበርሃማ ስፍራ ከደረቅ አየር ውሃ መሰብሰብ የሚያስችል አዲስ መሳርያ ተሰርቷል

በአሜሪካ ማሳቹሴትስ የተባለ የቴክኖሎጂ ተቋም በበርሃማ ስፍራ ከደረቅ አየር ውሃ መሰብሰብ የሚያስችል አዲስ ቴክኖሎጂ ማግኘታቸው እየተነገረ ነው።

የመጠጥ ውኃ ተደራሽነት በመላው ዓለም በተለይም በጣም ዝቅተኛ የእርጥበት መጠን ባለባቸው ደረቃማ አካባቢዎች አሳሳቢ እየሆነ ነው።

ተመራማሪዎች ግን ይህንን ችግር የሚፈታ አዲስ ቴክኖሎጂ ይዘው መምጣቻው ነው የተነገረው።

ለዚህም ቴክኖሎጂው ከ10 በመቶ በታች በሆነ እጅግ ዝቅተኛ እርጥበት ባለው አካባቢ ውሃን መያዝ እንደሚችል መረጋገጡ ተገልጿል።

ይህም መሳርያው የበርካታ ሰዎችን ችግር በመቅረፍ ህይወታቸው በማሻሻል የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለው ታምኖበታል።

በፀሀይ ሀይል የሚንቀሳቀሰው አዲሱ ቴክኖሎጂ አስፈለጊውን ግብዓት አሟልቶ ወደ ስራ ሲገባ፥ በሙከራ ላይ ከሰበሰበው ሶስት እጥፍ ውሃ መሰብሰብ የሚያስችል አቅም እንደሚኖረው ተነግሯል።

በዚህም ከፍተኛ የፀሀይ ሙቀትን የሚፈልግ በመሆኑ ተመራማሪዎቹ በቀጣይ ባዮፊል እና ሌሎች የሀይል አማራጮችን ለመጠቀም እየሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል።

በመሳሪያው የሚሰበሰበው ውሃ ጥራቱ የተጠበቀ ሲሆን፥ ምንም አይነት ተጨማሪ ማጣራት ሂደት አያስፈልገውም ነው የተባለው።

በመጨዎቹ ጊዜያትም በአለም ያለውን የውሃ እጥረት ለመቅረፍ የተሻለ ቴክኖሎጂ መፍጠር የሚቻልበት እድል እንዳለ ተነግሯል።

ምንጭ፦ fossbytes.com

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram