fbpx

በቀላሉ አስደናቂ ዳሌ እንዲኖርሽ የሚያደርጉ ቀላል የቤት ውስጥ እንቅስቃሴ

ዳሌና ቁንጅና ( ዳሌ ምንድነው? )
ውበት እንደተመልካቹ ነው። ውበት እንደ አካባቢው ነው። ውበት ልዩ ልዩ ነው። ለምእራባውያን ውበት ቅጥነት ነው። ለአፍሪካውያን ደግሞ ውበት ዳሌ ነው። *** ዳሌ ማለት ቂጥ በጨዋ ቋንቋ ተቆላምጦ ሲጠራ ነው። እኛ ኢትዮጵያውያኖች እንደተቀሩት አፍሪካውያን ወንድሞቻችን ዳሌን እናደንቃለን፤ ዳሌን እናፈቅራለን፤ ዳሌን እንመኛለን፤ ስለ ዳሌ ስንገጥም፤ ስለ ዳሌ ስንዘፍንና ዳሌን ስንመኝ ኖረናል። የፈረንጅ፤ የእሲያ ወይም የላቲን ሴቶች እንደ አፍሪካውያን ሴቶች ቆንጆ ዳሌ የላቸውም። ከአፍሪካውያን ደግሞ እንደ ኢትዮጵያውያን ሴቶች አይነት የተዋበ የተሞናሞነ ዳሌ የትም የለም። ኢትዮጵያውያን ሴቶች በጣም ትልቅ ያልሆነ፤ በጣም ልጥፍ ያላለ ሆኖም ግን ቦታ ቦታውን የያዘ ቆንጆ ዳሌ ባለቤት ናቸው። አረቡ፤ ነጩ፤ ጥቁሩ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ሲያይ ለሃጩ የሚዝረበረበው በሌላ ምክኒያት ሳይሆን በዋነኛነት በዳሌያቸው ነው። በእርግጥ የአበሻ ወንድ ዳሌ ያደንቃል። ዳሌ ይወዳል።

አንድ ጓደኛዬ <<ሴቶች በሁለት ይከፈላሉ>> ይላል ። <<እነሱም ፉንጋ ሴቶችና ዳሌ ያላቸው ሴቶች ናቸው>> ይላል። ይህ አባባሉ ዋዛ ቢመስልም ግን እውነትነት እንዳለው የሚታወቀው የሃበሻን ዘፈኖችን በማዳመጥ ነው። ሃበሻ ስለ ዳሌ ያለውን ፍቅር ለዘመናት ሲዘፍን ኖሮዋል። የሴቶች ቁንጅና በተገለጸባቸው ዘፈኖች በአብዛኛው ውስጥ ስለ ዳሌ ተዘፍኗል። አብዛኛው የሃበሻ ወንድ በመንገድ ላይ ሲሄድ ቆንጆ ዳሌ ያላት ሴት አጠር ያለ ቀሚስ ለብሳ ስታልፍ ዞር ብሎ ያያል። ቄሶች እንኳን ሳይቀሩ ዞር ብለው አይተው <<አይ ስምንተኛው ሺ ማለታቸው አይቀርም>>። ፓስተሮችም ቢሆን ዞር ብለው ካዩ በኋላ <<በየሱስ ስም ጊዜያችን እንዴት ተበላሸ>> ይላሉ። ለነገሩ ይሄ አፍቅሮተ ዳሌ የኢትዮጵያውያን ወንዶች ብቻ አይደለም። ጥቁር አሜሪካውያን ወንዶች ለዳሌ የተለየ ፍቅር አላቸው። ይህን ፍቅራቸውን በዘፈናቸው፤ በስእላቸውና በስነጽሁፋቸው ውስጥ ይገልጹታል። በዚህ ሳምንት ውስጥ እንኳን በጥቁር አሜሪካውያን የሂፕ ሆፕ ስልት ከተዘፈኑና ገበያውን ከሚመሩት ምርጥ አስር ዘፈኖች ውስጥ ስምንቱ ስለ ዳሌ የሚያወሩ ናቸው።

Booty ይሉታል እነሱ። ጥቁሮች እንደ እኛ ሸፈንፈን አድርገው አይገልጹትም። አምጪው፤ አንቀጥቅጪው እያሉ ፍላጎታቸው ይገልጻሉ። የሂፕ ሆፕ ስልት ከሚከተሉት ያገራችን ዘፋኞች ውስጥ አሁን አሁን አንቀጥቅጪው የሚሉ ዘፈኖች በብዛት እይተደመጡ ነው። የቴዲ ዮ <<ጉራጌ ቶን>> ዘፈን ውስጥ <<ሴቶች አንቀጥቅጡት ቀጥ>> የሚለውን ሂፕ ሃፕ ዘፈንና ሌሎች በርካታ የሃበሻ ዘፈን ክሊፖች እዚህ ላይ ዋቢ ማድረግ ይቻላል። ምንም እንኳን ከሁሉም ሕዝቦች በተለየ ሁኔታ ቆንጆ ዳሌ ያላቸው ጥቁሮች ቢሆኑም መላው የአዳም ዘር ግን ዳሌ እንደሚወድ አይካድም። ይህንን አፍቅሮተ ዳሌ የኢቮሉሽን ሳንይንቲስቶች ዘር ከማብዛት ፍላጎት ጋር ያያይዙታል።

ዳሌዋ ሰፊ የሆነች ሴት ልጆችን በቀላሉ መውለድ ስለምትችል ወንዶቹ ሳያውቁት ይሳቡለታል ይላሉ። ዘር ማብዛት ማን ይጠላል? Survival of the fittest!!! በዚህ ምክኒያት እንደ ዳይኖሰር ከመጥፋት ተርፈን ይሆናል እንደማለት ነው። አሁን …. አሁን ግን ፈረንጆቹ የዳሌን ውበትነት እየሻሩት ይመስላል። ለፈረንጆች <ውበት ማለት ቅጥነት ነው> የሚል ያልተጻፈ ሕግ የተደነገገ ይመስላል። ለነገሩ የፈረንድ ሴቶች ወፈሩ ማለት የጥጥ ፍራሽ ሊሰፋ ሲበተን እንደማለት ናቸው። ይዝረከረካሉ። ስለዚህ ፈረንጆች ቅጥነት ቢያደንቁ አይገርምም። አበሻ ግን ምን በወጣው? ታዲያ ዛሬ …. ዛሬ ሞዴል ሴቶች ከሚገባው በታች ቀጭን እንዲሆኑ ይጠበቅባቸዋል። በዚህ ምክኒያት አብዛኛዎቹ ሱፐር ሞዴሎች ከሚገባቸው በላይ እየቀጠኑ ለከፋ በሽታ እየተዳረጉ ነው። ፈረንሳይ ውስጥ ያሉ የፋሽን ኢንደስትሪ ባለቤቶች ሞዴሎችን ከሚገባው በታች እንዲቀጥኑ እያስገደዱ ለበሽታ እንዳያጋልጡ ለመከላከል የፈረንሳይ መንግስት አዲስ ሕግ እስከማረቀቅ ደርሷል። ይሄ ረቂቅ ሕግ ሞዴል ሴቶች ከተወሰነ ክብደበት በታች እንዲቀንሱ የሚያስገድዱ ድርጅቶችን ፈቃድ የሚሰርዝ ነው።

የሞዴሎች ቅጥነት ሲባል የወገባቸው እና የዳሌያቸው መጠን ከደብል ዜሮ በታች እንዲሆን የሚያዙ ናቸው። በዚህ አለም አቀፍ የፋሽን ገበያ ምክንያትዘመናዊ ነኝ የምትል ሴት ሁሉ መቅጠን እንደ ግዴታ ማየት ጀምራለች። ይሄን የፈረንጆች ሚዛን ተከትሎ የእኛ አገር ቆነጃጅትም በሁለት ጽንፍ ግራ የተጋቡ ይመስላል። በአንድ በኩል መቅጠን ውበትና ዘመናዊነት እንደሆነ እያሰቡ ለመቅጠን ሲታገሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ዛሬም ድረስ የሃበሻ ወንዶች አይን የሚከተለው የሚነጥር ዳሌ መሆኑ ግራ ያጋባቸዋል። በዚህ ምክኒያት ብዙ ሴቶች ስፓርት ሰርተው ወይም ምግባቸው አስተካክለው መቅጠን እየቻሉ ውፍረታቸውን ይዘው ይቀጥላሉ። ምክኒያቱም ዛሬም ድረስ የሃበሻ ወንዶች አንገት እየተጠመዘዘ የሚያየው እና በፌስ ቡክ ላይ ሳይቀር WOW … ዋው…. ዊው የሚሉት ባለ ዳሌ ሴቶችን እንጂ አይናቸው የሚያምር… ወይም ጸጉራቸው ረጅሞቹን አይደለም። እነሆ የአበሻ ወንዶች የሚፈልጉት <ዳሌ> ከሆነ፤ የአበሻ ሴቶችም ጥሩ ዳሌ ካላቸው የፈረንጆችን ውበት መኮረጅ ምን ያስፈልጋል? ሰው ባለው ይሸናል እንዲል ትግሬ እኛም ባለን ብንኮራስ?

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram